ስለ እኔ ሰውነታቸውን ለመከራ አሳልፈው ሰጥተዋልና፤ የማመሰግናቸውም እኔ ብቻ አይደለሁም፤ ከአሕዛብ ያመኑ ምእመናን ሁሉ ያመሰግኑአቸዋል እንጂ።
መሳፍንት 9:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቴስ ለእናንተ እንደ ተጋደለ፥ በፊታችሁም ሰውነቱን ለሞት አሳልፎ እንደ ሰጠ፥ ከምድያምም እጅ እንደ አዳናችሁ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቴ ለእናንተ መዋጋቱን፣ ከምድያማውያን እጅ ሊያድናችሁ ሕይወቱን መስጠቱን ዐሰባችሁ ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቴ ለእናንተ መዋጋቱን፥ ከምድያማውያን እጅ ሊያድናችሁ ሕይወቱን መስጠቱን አሰባችሁ ማለት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቴ ለእናንተ እንደ ተዋጋና እናንተንም ከምድያማውያን እጅ ለማዳን ሲል ሕይወቱን በአደጋ ላይ ጥሎ እንደ ነበረ አስታውሱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቴ ስለ እናንተ ተጋድሎ ነበርና፥ ከምድያምም እጅ ሊያድናችሁ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶ ነበርና፥ |
ስለ እኔ ሰውነታቸውን ለመከራ አሳልፈው ሰጥተዋልና፤ የማመሰግናቸውም እኔ ብቻ አይደለሁም፤ ከአሕዛብ ያመኑ ምእመናን ሁሉ ያመሰግኑአቸዋል እንጂ።
የሚያድን እንደሌለም ባየሁ ጊዜ ሰውነቴን በእጄ አሳልፌ ለሞት በመስጠት ወደ አሞን ልጆች ተሻገርሁ፤ እግዚአብሔርም በፊቴ ጣላቸው፤ ለምንስ ዛሬ ልትወጉኝ ወደ እኔ መጣችሁ?” አላቸው።
አሁን እንግዲህ አቤሜሌክን በማንገሣችሁ እውነትንና ቅንነትን አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥ ለይሩበኣልም፥ ለቤቱም በጎ አድርጋችሁ እንደሆነና እንደ እጁም ዋጋ መጠን ለእርሱ የተገባውን አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥
እናንተም ዛሬ በአባቴ ቤት ተነሥታችኋል፤ ሰባ የሆኑትን ልጆቹንም በአንድ ድንጋይ ላይ ገድላችኋል፤ ወንድማችሁም ስለሆነ የዕቅብቱን ልጅ አቤሜሌክን በሰቂማ ሰዎች ላይ አንግሣችኋል፥
ነፍሱንም በእጁ ጥሎ ፍልስጥኤማዊዉን ገደለ፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ታላቅ መድኀኒት አደረገ፤ እስራኤልም ሁሉ አይተው ደስ አላቸው፤ በከንቱ ዳዊትን ትገድለው ዘንድ ስለምን በንጹሕ ደም ላይ ትበድላለህ?”