የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ፥ “የሊባኖስ ኵርንችት፦ ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው ብሎ ወደ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም አውሬ አልፎ ኵርንችቱን ረገጠ።
መሳፍንት 9:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዶግም ዛፎቹን፦ በእውነት እኔን በእናንተ ላይ ካነገሣችሁኝ እሳት ከዶግ ወጥቶ የሊባኖስን ዝግባ ካልበላው ከጥላዬ በታች ታርፉ ዘንድ ኑ አለቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእሾኽ ቍጥቋጦውም ዛፎቹን፣ ‘በርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾኽ ቍጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ!’ አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእሾኽ ቊጥቋጦውም ዛፎቹን፥ “በእርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾ ቊጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእሾኽ ቊጥቋጦም ‘በእርግጥ ንጉሥ ልታደርጉኝ ከፈለጋችሁ፥ ኑና በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ከእሾኻማዎቹ ቅርንጫፎቼ እሳት ወጥቶ የሊባኖስ ዛፍን ያቃጥላል’ ሲል መለሰላቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሾሁም ዛፎችን፦ በእውነት እኔን በእናንተ ላይ ታነግሡኝ እንደ ሆነ ኑ ከጥላዬ በታች ተጠጉ። እንዲሁም ባይሆን እሳት ከእሾህ ይውጣ፥ የሊባኖስንም ዝግባ ያቃጥል አላቸው። |
የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ፥ “የሊባኖስ ኵርንችት፦ ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው ብሎ ወደ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም አውሬ አልፎ ኵርንችቱን ረገጠ።
ኀይላቸውም እንደ መቃ መስዬ፥ ሥራቸውም እንደ ጠለሸት ይሆናል፤ ኃጥአንና ዐማፅያንም አብረው ይቃጠላሉ፤ እሳቱንም የሚያጠፋላቸው ያጣሉ።”
አንተም በመልእክተኞችህ በኩል እንዲህ ብለህ እግዚአብሔርን ተገዳደርኸው፦ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባኖስ ራስ ወጥቻለሁ፤ ረዣዥሞቹንም ዝግባዎች፥ የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፤ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ዱሩ እገባለሁ፤
ሬስ። ስለ እርሱ፥ “በአሕዛብ ውስጥ በጥላው በሕይወት እንኖራለን” ያልነው፥ በእግዚአብሔር የተቀባ፥ የሕይወታችን እስትንፋስ፥ በወጥመዳቸው ተያዘ።
ከተመረጡት ጫፎችዋም በትር እሳት ወጣች፤ ፍሬዋንም በላች፤ የነገሥታትም በትር ይሆን ዘንድ የበረታ በትር የለባትም።” ይህ ሙሾ ነው፤ ለልቅሶም ይሆናል።
እነሆ አሦር ጫፉ እንደ ተዋበ፥ ችፍግነቱ ጥላ እንደ ሰጠ፥ ቁመቱም እንደ ረዘመ፥ ራሱም ወደ ደመናዎች እንደ ደረሰ እንደ ሊባኖስ ዝግባ ነበረ።
እርስዋም ከዘር ሁሉ ታንሳለች፤ በአደገች ጊዜ ግን፥ ከአታክልቶች ትበልጣለች የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።”
አሁን እንግዲህ አቤሜሌክን በማንገሣችሁ እውነትንና ቅንነትን አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥ ለይሩበኣልም፥ ለቤቱም በጎ አድርጋችሁ እንደሆነና እንደ እጁም ዋጋ መጠን ለእርሱ የተገባውን አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥
እንዲህ ባይሆን ግን ከአቤሜሌክ እሳት ትውጣ፤ የሰቂማንም ሰዎች፥ የመሐሎንንም ቤት ትብላ፤ ያም ባይሆን ከሰቂማ ሰዎች ከመሐሎንም ቤት እሳት ትውጣ፤ አቤሜሌክንም ትብላው።”
አቤሜሌክም ከእርሱም ጋር ያሉት ሠራዊት በከተማዪቱ መግቢያ በር ሸምቀው ቆሙ። እነዚያ ሁለቱ ሠራዊት ግን ወደ ጫካው ተበትነው አጠፉአቸው።
ሕዝቡም ሁሉ እንዲሁ እያንዳንዳቸው የዛፉን ቅርንጫፎች ቈረጡ፤ አቤሜሌክንም ተከትለው በምሽጉ ዙሪያ አኖሩአቸው፤ ምሽጉንም በላያቸው በእሳት አቃጠሉት፤ የሰቂማም ግንብ ሰዎች ሁሉ ደግሞ አንድ ሺህ የሚያህሉ ወንድና ሴት ሞቱ።