መሳፍንት 8:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፋኑሄልንም ግንብ አፈረሰ፤ የከተማዪቱንም ሰዎች ገደላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም በጵኒኤል ያለውን የከተማ መጠበቂያ ግንብ አፈረሰ፤ የከተማዪቱንም ሰዎች ገደለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም በጵኒኤል ያለውን የከተማ መጠበቂያ ግንብ አፈረሰ፤ የከተማይቱንም ሰዎች ገደለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጵኑኤል ያለውንም የከተማ መጠበቂያ ግንብ አፈረሰ፤ በከተማይቱ ውስጥ የሚገኙትንም ወንዶች ሁሉ ገደለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጵኒኤልንም ግንብ አፈረሰ፥ የከተማይቱንም ሰዎች ገደላቸው። |
ዛብሄልንና ስልማናን፥ “በታቦር የገደላችኋቸው ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ?” አላቸው፤ እነርሱም፥ “እንዳንተ ያሉ ነበሩ፤ አንተንም ይመስሉ ነበር፤ መልካቸውም እንደ ነገሥት ልጆች መልክ ነበረ” ብለው መለሱለት።