መሳፍንት 6:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም ሆነ፤ በነጋው ማልዶ ተነሣ፤ ጠጕሩንም ጨመቀው፤ ከጠጕሩም የተጨመቀው ጠል አንድ መንቀል ሙሉ ውኃ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደዚሁ ሆነ፤ ጌዴዎን በማግስቱም ጧት ማልዶ ተነሣ፤ ባዘቶውንም ሲጨምቅ የወጣው ውሃ አንድ ገበቴ ሞላ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደዚሁም ሆነ፤ ጌዴዎን በማግስቱ ጠዋት ማልዶ ተነሣ፤ ባዘቶውንም ሲጨምቅ የወጣው ውሃ አንድ ቆሬ ሞላ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልክ እርሱ እንዳለውም ሆነለት፤ ጌዴዎን ጧት በማለዳ በተነሣ ጊዜ የበግ ጠጒሩን ባዘቶ ሲጨምቀው በአንድ መቅጃ የሚሞላ ውሃ ከውስጡ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም ሆነ፥ በነጋውም ማልዶ ተነሣ፥ ጠጉሩንም ጨመቀው፥ ከጠጉሩም የተጨመቀው ጠል ቆሬ ሙሉ ውኃ ሆነ። |
ካህኑም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል፤ አንገቱንም ይቈርጠዋል፥ በመሠዊያውም ላይ ያኖረዋል። ደሙንም በመሠዊያው አጠገብ ያንጠፈጥፈዋል፤
እነሆ! በዐውድማዉ ላይ የተባዘተ የበግ ጠጕር አኖራለሁ፤ በጠጕሩ ብቻ ላይ ጠል ቢሆን በምድሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን፥ እንደ ተናገርህ የእስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ እንደምታድናቸው አውቃለሁ” አለ።
ጌዴዎንም እግዚአብሔርን አለው፥ “በቍጣህ አትቈጣኝ፤ ደግሞ አንዲት ነገር ልናገር፤ ጠጕሩ ብቻውን ደረቅ ይሁን፤ በምድሩም ላይ ጠል ይውረድ።”