የኔር ልጅ የይሩበዓልን ልጅ አቤሜሌክን ማን ገደለው? አንዲት ሴት ከቅጥር ላይ የወፍጮ መጅ ጥላበት የሞተ አይደለምን? ስለምን ወደ ቅጥሩ እንደዚህ ቀረባችሁ? አንተም፦ ባሪያህ ኬጤያዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ በለው።”
መሳፍንት 6:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያች ቀንም መሠዊያዉን አፍርሶአልና በዓል ከእርሱ ጋር ይሟገት ሲል ጌዴዎንን ይሩበኣል ብሎ ጠራው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም፣ “መሠዊያውን አፍርሶበታልና ራሱ በኣል ይሟገተው” ሲሉ በዚያ ዕለት ጌዴዎንን፣ “ይሩባኣል” ብለው ጠሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም፥ “መሠዊያውን አፍርሶበታልና ራሱ በኣል ይሟገተው” ሲሉ በዚያ ዕለት ጌዴዎንን፥ “ይሩበኣል” ብለው ጠሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢዮአስ “ፈራርሶ የወደቀው የእርሱ መሠዊያ ስለ ሆነ እስቲ ይችል እንደ ሆነ ባዓል ራሱን ይከላከል፤” ለማለት ፈልጎ፥ ለጌዴዎን ይሩባዓል የሚል ስም አወጣለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም በዚያ ቀን፦ መሠዊያውን አፍርሶአልና በኣል ከእርሱ ጋር ይምዋገት ብሎ ጌዴዎንን፦ ይሩበኣል ብሎ ጠራው። |
የኔር ልጅ የይሩበዓልን ልጅ አቤሜሌክን ማን ገደለው? አንዲት ሴት ከቅጥር ላይ የወፍጮ መጅ ጥላበት የሞተ አይደለምን? ስለምን ወደ ቅጥሩ እንደዚህ ቀረባችሁ? አንተም፦ ባሪያህ ኬጤያዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ በለው።”
ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ናቸው፤ እንደ ኢየሩሳሌምም መንገዶች ቍጥር ለነውረኛ ነገር ለበዓል ታጥኑባቸው ዘንድ መሠዊያዎችን አድርጋችኋል።
እስራኤልን በምድረ በዳ እንደ አለ ወይን ሆኖ አገኘሁት፤ አባቶቻችሁንም በመጀመሪያዋ ዓመት እንደ በለስ በኵራት ሆነው አየኋቸው፤ እነርሱ ግን ወደ ብዔልፌጎር መጡ፤ ለነውርም ተለዩ፤ እንደ ወደዱትም ርኩስ ሆኑ።
ኢዮአስም በእርሱ ላይ የተነሡበትን ሁሉ፥ “ለበዓል እናንተ ዛሬ ትበቀሉለታላችሁን? ወይስ የበደለውን ትገድሉለት ዘንድ የምታድኑት እናንተ ናችሁን? እርሱ አምላክ ከሆነስ የበደለው እስከ ነገ ድረስ ይሙት። መሠዊያዉንም ያፈረሰውን እርሱ ይበቀለው” አላቸው።
ጌዴዎን የተባለውም ይሩበኣል ከእርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ማልደው ተነሡ፤ በአሮኤድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ፤ የምድያምም ሰፈር ከእነርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ።
እርሱም ለእስራኤል በጎ ነገርን ሁሉ እንዳደረገ መጠን፥ እነርሱ ይሩበኣል ለተባለው ለጌዴዎን ቤት ወረታ አላደረጉም።
እግዚአብሔርም ይሩበኣልን፥ ባርቅንም፥ ዮፍታሔንም፥ ሳሙኤልንም ላከ፤ በዙሪያችሁም ካሉት ከጠላቶቻችሁ እጅ አዳኑአችሁ፤ ተዘልላችሁም ተቀመጣችሁ።