እሳትም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወረደች፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ እንጨቱንም፥ ድንጋዮቹንም በላች፤ በጕድጓዱም ውስጥ ያለውን ውኃ፥ አፈሩንም ላሰች።
መሳፍንት 6:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መልአክ በእጁ ያለውን በትሩን ዘርግቶ ሥጋዉንና የቂጣዉን እንጎቻ አስነካ፤ እሳትም ከድንጋዩ ውስጥ ወጥታ ሥጋዉንና የቂጣዉን እንጎቻ በላች። የእግዚአብሔርም መልአክ ከዐይኖቹ ተሰወረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልአኩም በያዘው በትር ጫፍ ሥጋውንና ቂጣውን ነካ፤ ከዐለቱም እሳት ወጥቶ ሥጋውንና ቂጣውን በላ፤ ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ ተሰወረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልአኩም በያዘው በትር ጫፍ ሥጋውንና ቂጣውን ነካ፤ ከዐለቱም እሳት ወጥቶ ሥጋውንና ቂጣውን በላ፤ ከዚያም የጌታ መልአክ ተሰወረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ቀረብ ብሎ በያዘው በትር ጫፍ ሥጋውንና እንጀራውን ነካ፤ እሳትም ከአለቱ ላይ ተነሥቶ ሥጋውንና እንጀራውን በላ፤ ከዚያም በኋላ መልአኩ ተሰወረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መልአክ በእጁ ያለውን የበትሩን ጫፍ ዘርግቶ ሥጋውንና የቂጣውን እንጎቻ አስነካ፥ እሳትም ከድንጋዩ ውስጥ ወጥቶ ሥጋውንና የቂጣውን እንጎቻ በላ። የእግዚአብሔርም መልአክ ከዓይኑ ተሰወረ። |
እሳትም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወረደች፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ እንጨቱንም፥ ድንጋዮቹንም በላች፤ በጕድጓዱም ውስጥ ያለውን ውኃ፥ አፈሩንም ላሰች።
ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱንም መሥዋዕት አቀረበ፤ እግዚአብሔርንም ጠራ፤ ከሰማይም ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ በእሳት መለሰለት፤ እሳቱም የሚቃጠለውን መሥዋዕት በላ።
ሰሎሞንም ይህን ጸሎት በፈጸመ ጊዜ እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውን ቍርባንና መሥዋዕቱን ሁሉ በላ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ቤቱን ሞላ።
እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ስቡንም በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው ተደነቁ፤ በግምባራቸውም ወደቁ።
ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው። መልአኩም ተአምራት አደረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም ይመለከቱ ነበር።
ነበልባሉም ከመሠዊያዉ ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በመሠዊያዉ ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም ተመለከቱ፤ በምድርም በግንባራቸው ወደቁ።
የእግዚአብሔርም መልአክ፥ “ሥጋውንና የቂጣውን እንጎቻ ወስደህ በዚህ ድንጋይ ላይ አኑር፤ መረቁንም አፍስስ” አለው። እንዲሁም አደረገ።