የሲሣራ እናት በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ በሰቅሰቅም ዘልቃ፦ ከሲሣራ የተመለሰ እንዳለ አየች፤ ስለምን ለመምጣት ሰረገላው ዘገየ? ስለምንስ የሰረገላው መንኰራኵር ቈየ? ብላ ጮኸች።
መሳፍንት 5:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብልሃተኞች ሴቶችዋ መለሱላት፤ እርስዋ ደግሞ ለራስዋ እንዲህ ብላ መለሰች፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብልኀተኞች ወይዛዝርቷም መለሱላት፤ እርሷ ግን ለራሷ እንዲህ አለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብልሃተኞች ሴቶችዋ መለሱላት፥ እርሷ ደግሞ ለራስዋ እንዲህ ብላ መለሰች፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበበኞች የሆኑ ወይዛዝሮችዋም መልስ ሰጡአት፤ በእርግጥ እርስዋ ለራስዋ መልስዋን አገኘች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብልሃተኞች ሴቶችዋ መለሱላት፥ እርስዋ ደግሞ ለራስዋ እንዲህ ብላ መለሰች፦ |
የሲሣራ እናት በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ በሰቅሰቅም ዘልቃ፦ ከሲሣራ የተመለሰ እንዳለ አየች፤ ስለምን ለመምጣት ሰረገላው ዘገየ? ስለምንስ የሰረገላው መንኰራኵር ቈየ? ብላ ጮኸች።
ምርኮውን ሲካፈል፥ በኀያላኑም ቸብቸቦ ላይ ወዳጆችን ሲወዳጅ ያገኙት አይደለምን? የሲሣራ ምርኮ በየኅብሩ ነበረ፤ የኅብሩም ቀለም የተለያየ ነበረ፤ የማረከውም ወርቀ ዘቦ ግምጃ በአንገቱ ላይ ነበረ።