አካዝያስም በሰማርያ በሰገነቱ ላይ ሳለ በዐይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እርሱም፥ “ሂዱ፥ ከዚህ ደዌ እድን እንደ ሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ጠይቁ” ብሎ መልእክተኞችን ላከ፤ እነርሱም ሊጠይቁለት ሄዱ።
መሳፍንት 5:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሲሣራ እናት በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ በሰቅሰቅም ዘልቃ፦ ከሲሣራ የተመለሰ እንዳለ አየች፤ ስለምን ለመምጣት ሰረገላው ዘገየ? ስለምንስ የሰረገላው መንኰራኵር ቈየ? ብላ ጮኸች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሲሣራ እናት በመስኮት ተመለከተች፤ በዐይነ ርግቡ ቀዳዳም ጮኻ ተጣራች፤ ‘ለምን ሠረገላው ሳይመጣ ዘገየ? የሠረገሎቹስ ድምፅ ለምን ጠፋ?’ አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመስኮት ሆና ተመለከተች፥ የሲሣራ እናት በሰቅሰቅ ዘልቃ፦ “ስለምን ለመምጣት ሠረገላው ዘገየ? ስለ ምንስ የሠረገላው መንኰራኵር ቈየ?” ብላ ጮኸች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሲሣራ እናት በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ በዐይነ ርግብ ቀዳዳም አተኲራ አየች፤ “የልጄ ሠረገላ ለምን ዘገየ? የሠረገላዎቹ ፈረሶች የኮቴ ድምፅስ ለምን ዘገየ?” ስትል ጠየቀች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመስኮት ሆና ተመለከተች፥ የሲሣራ እናት በሰቅሰቅ ዘልቃ፦ ስለ ምን ለመምጣት ሰረገላው ዘገየ? ስለ ምንስ የሰረገላው መንኰራኵር ቈየ? ብላ ጮኸች። |
አካዝያስም በሰማርያ በሰገነቱ ላይ ሳለ በዐይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እርሱም፥ “ሂዱ፥ ከዚህ ደዌ እድን እንደ ሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ጠይቁ” ብሎ መልእክተኞችን ላከ፤ እነርሱም ሊጠይቁለት ሄዱ።
ልጅ ወንድሜ በቤቴል ተራሮች ላይ ሚዳቋን ወይም የዋሊያን እንምቦሳ ይመስላል፤ እነሆ፥ በመስኮቶች ሲጐበኝ፥ በዐይነ ርግብም ሲመለከት፥ እርሱ ከቅጥራችን በኋላ ቆሞአል።
እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ። እነሆ ገበሬው የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እስኪቀበል ድረስ እርሱን እየታገሠ የከበረውን የመሬት ፍሬ ይጠብቃል።
እግዚአብሔርም ሲሣራን፥ ሰረገሎቹንም ሁሉ፥ ሠራዊቱንም ሁሉ ከባርቅ ፊት በሰይፍ ስለት አስደነገጣቸው፤ ሲሣራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ።