መሳፍንት 5:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሳኮርም አለቆች ከዲቦራ ጋር ነበሩ፤ ይሳኮርም እንደ ባርቅ ነበረ፤ ከእግሩ በኋላ ወደ ሸለቆው ቸኮሉ፤ በሮቤል ፈሳሾች አጠገብ ብዙ የልብ ማመንታት ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሳኮር መሳፍንት ከዲቦራ ጋራ ነበሩ፤ ይሳኮርም ራሱ ወደ ሸለቆው ከኋላው በመከተል፣ ከባርቅ ጋራ ነበረ። በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብ ምርምር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሳኮርም አለቆች ከዲቦራ ጋር ነበሩ፥ ይሳኮርም እንደ ባራቅ ነበረ፥ ከእግሩ በኋላ ወደ ሸለቆው ቸኰሉ፥ በሮቤል ፈሳሾች አጠገብ ብዙ የልብ ማመንታት ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሳኮር መሪዎች ከዲቦራ ጋር መጡ፤ አዎ፥ ይሳኮርም ባራቅም መጡ፤ ወደ ሸለቆው ተከተሉት፤ ነገር ግን የሮቤል ነገድ ለሁለት ተከፈለ፤ ለመምጣት ወይም ላለመምጣት አመነታ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሳኮርም አለቆች ከዲቦራ ጋር ነበሩ፥ ይሳኮርም እንደ ባርቅ ነበረ፥ ከእግሩ በኋላ ወደ ሸለቆው ቸኰሉ፥ በሮቤል ፈሳሾች አጠገብ ብዙ የልብ ማመንታት ነበረ። |
እስራኤልም የሚገባውን ያደርግ ዘንድ ዘመኑን የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
እኛ ግን በመርከብ ሆነን ወደ አሶስ ሄድን፤ ከዚያ ጳውሎስን ልንቀበለው እንሻ ነበርና፤ እንደዚሁ በእግር እንደሚመጣ ነግሮን ነበርና ተቀበልነው።
ለእግዚአብሔር የሚገባ ቅንዐት እቀናላችኋለሁና፤ ወደ እርሱ አቀርባችሁ ዘንድ ለአንዱ ንጹሕ ድንግል ሙሽራ ለክርስቶስ አጭቻችኋለሁና።
ዲቦራም ባርቅን፥ “እግዚአብሔር ሲሣራን በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥበት ቀን ዛሬ ነውና ተነሣ፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር በፊትህ ይሄዳል” አለችው። ባርቅም ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከትለውት ከታቦር ተራራ ወረደ።
ዲቦራም ልካ ከቃዴስ ንፍታሌም የአቢኒሔምን ልጅ ባርቅን ጠርታ እንዲህ አለችው፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ያዘዘህ አይደለምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአንተም ጋር ከንፍታሌምና ከዛብሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤
መንጎች ሲያፍዋጩ ለመስማት፥ በበጎች ጉረኖ መካከል ለምን ተቀመጥህ? በሮቤል ፈሳሾች አጠገብ ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ።