አሜሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ከነበረው ሰይፍ አልተጠነቀቀም ነበር፤ ኢዮአብም ሆዱን ወጋው፤ አንጀቱንም በምድር ላይ ዘረገፈው፤ ሁለተኛም አልወጋውም፤ ሞተም። ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳም የቢኮሪን ልጅ ሳቡሄን አሳደዱ።
መሳፍንት 3:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ ናዖድን ሁለቱ እጆቹ ቀኝ የሆኑለትን ሰው አዳኝ አስነሣላቸው፤ የእስራኤልም ልጆች በእርሱ እጅ ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎም እጅ መንሻ ላኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን እንደ ገና ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ ግራኙን ናዖድን ነጻ እንዲያወጣቸው አስነሣው። እስራኤላውያን ናዖድን ግብር አስይዘው ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያን እንደገና ወደ ጌታ ጮኹ፤ ጌታም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ፥ ግራኙን፥ ኤሁድን ነጻ እንዲያወጣቸው አስነሣው። እስራኤላውያን ኤሁድን ግብር አስይዘው ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ነገድ ግራኝ የነበረውን የጌራን ልጅ ኤሁድን አዳኝ አድርጎ አስነሣቸው፤ የእስራኤል ሕዝብ ኤሁድን ግብር አስይዘው ወደ ሞአብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ ናዖድን ግራኙን ሰው አዳኝ አስነሣላቸው፥ የእስራኤልም ልጆች በእርሱ እጅ ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎም ግብር ላኩ። |
አሜሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ከነበረው ሰይፍ አልተጠነቀቀም ነበር፤ ኢዮአብም ሆዱን ወጋው፤ አንጀቱንም በምድር ላይ ዘረገፈው፤ ሁለተኛም አልወጋውም፤ ሞተም። ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳም የቢኮሪን ልጅ ሳቡሄን አሳደዱ።
ቀስተኞችም ነበሩ፤ በቀኝና በግራም እጃቸው ድንጋይ ሊወነጭፉ፥ ፍላጻም ሊወረውሩ ይችሉ ነበር፤ ከብንያም ወገን የሳኦል ወንድሞች ነበሩ።
ከእነርሱም እያንዳንዱ ገጸ በረከቱን፥ የወርቅንና የብርን ዕቃ፥ ልብስንና የጦር መሣሪያን፥ ሽቱውንም፥ ፈረሶችንና በቅሎዎችን እየያዘ በየዓመቱ ያመጣ ነበር።
ሕዝቅያስንም አትስሙ፤ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ በሕይወት ልትኖሩ ብትወድዱ ሁላችሁ ወደ እኔ ውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ትበላላችሁ፤ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ትጠጣላችሁ፤
ከእነዚያም ሕዝብ ሁሉ ሰባት መቶ የተመረጡ፥ ሁለቱም እጆቻቸው ቀኝ የሆኑላቸው ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህም ሁሉ ድንጋይ ይወነጭፉ ነበር፤ አንዲት ጠጕርስ እንኳ አይስቱም ነበር።
የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። እግዚአብሔርም ለእስራኤል መድኀኒትን አስነሣላቸው። የካሌብ የታናሽ ወንድሙ የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያልም አዳናቸው፤ ለእርሱም ታዘዙለት።
የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና፥ የእስራኤልንም ልጆች ሃያ ዓመት እጅግ ያስጨንቃቸው ነበር።