መሳፍንት 21:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ጊዜ የብንያም ልጆች ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፤ የእስራኤልም ልጆች ከኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ያዳኑአቸውን ሴቶች ሰጡአቸው። በዚህም ተስማሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በዚህ ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፤ ከመገደል የተረፉትንም የኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ሰጧቸው፤ ይሁን እንጂ የሴቶቹ ቍጥር ለሁሉም የሚበቃ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በዚህን ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፤ ከመገደል የተረፉትንም የኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ሰጧቸው፤ ይሁን እንጂ የሴቶቹ ቊጥር ለሁሉም የሚበቃ አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብንያማውያንም ተመልሰው መጡ፤ ሌሎቹም እስራኤላውያን ከሞት በመትረፍ ከያቤሽ ተማርከው የመጡትን ልጃገረዶች ሰጡአቸው፤ ነገር ግን ቊጥራቸው ተመጣጣኝ ሆኖ አልተገኘም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ጊዜ የብንያም ልጆች ተመለሱ፥ ከኢያቢስ ገለዓድም ሴቶች ያዳኑአቸውን ሴቶች አገቡአቸው። ነገር ግን የሚበቁ ሴቶች አላገኙም። |
በኢያቢስ ገለዓድ በሚኖሩ መካከልም ወንድ ያላወቁ አራት መቶ ቆነጃጅት ደናግልን አገኙ፤ በከነዓንም ሀገር ወዳለችው ወደ ሴሎ ወደ ሰፈሩ አመጡአቸው።
አባቶቻቸውና ወንድሞቻቸውም ሊጣሉአችሁ ወደ እኛ በመጡ ጊዜ፦ ስለ እኛ ማሩአቸው፥ እኛ ሚስት ለያንዳንዳቸው በሰልፍ አልወሰድንላቸውምና፥ እናንተም በደል ይሆንባችሁ ስለ ነበር አላጋባችኋቸውምና፥” እንላቸዋለን።
እነርሱም፥ “ከእስራኤል ነገድ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ ያልወጣ ማን ነው?” አሉ። እነሆም፥ ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ ሰፈሩ ወደ ጉባኤው ማንም አልወጣም ነበር።