መሳፍንት 21:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምታደርጉትም ይህ ነው፤ ወንዱን ሁሉ፥ ወንድ የሚያውቁትንም ሴቶች ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ፤ ደናግሉን ግን አትግደሉአቸው፤” ብለው አዘዙአቸው፤ እንዲሁም አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “እንግዲህ የምታደርጉት ይህ ነው፤ ወንዱን በሙሉ እንዲሁም ድንግል ያልሆኑትን ሴቶች ሁሉ ግደሉ” አሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፥ “እንግዲህ የምታደርጉት ይህ ነው፤ ወንዱን በሙሉ እንዲሁም ድንግል ያልሆኑትን ሴቶች ሁሉ ግደሉ” አሏቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንዶችን ሁሉና ከወንድ ጋር የተገናኙትን ሴቶች ሁሉ ግደሉ ብለው አዘዙአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምታደርጉትም ይህ ነው፥ ወንዱን ሁሉ፥ ከወንድ ጋር የተኛችይቱንም ሴት ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ ብለው አዘዙአቸው። |
በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ወሰድን፤ ከተማውንም ሁሉ፥ ሴቶችንም፥ ሕፃኖችንም አጠፋን፤ አንዳችም የሸሸ በሕይወት አላስቀረንም፥
በኢያቢስ ገለዓድ በሚኖሩ መካከልም ወንድ ያላወቁ አራት መቶ ቆነጃጅት ደናግልን አገኙ፤ በከነዓንም ሀገር ወዳለችው ወደ ሴሎ ወደ ሰፈሩ አመጡአቸው።