La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች፥ “ከእኛ ማንም ሰው ሴት ልጁን ለብ​ን​ያም ልጆች በጋ​ብቻ አይ​ስጥ” ብለው በመ​ሴፋ ተማ​ማሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እስራኤላውያን በምጽጳ፣ “ከእኛ አንድም ሰው ሴት ልጁን በጋብቻ ለብንያማውያን መዳር የለበትም” በማለት ተማምለው ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እስራኤላውያን በምጽጳ፥ “ከእኛ አንድም ሰው ሴት ልጁን በጋብቻ ለብንያማውያን መዳር የለበትም” በማለት ተማምለው ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስራኤላውያን በምጽጳ በተሰበሰቡ ጊዜ “ከእኛ መካከል ማንም ሰው ሴት ልጁን ለብንያማዊ መዳር የለበትም” በማለት ተማምለው ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤልም ሰዎች፦ ከእኛ ማንም ሰው ልጁን ለብንያም ልጆች አያጋባ ብለው በምጽጳ ተማምለው ነበር።

Ver Capítulo



መሳፍንት 21:1
19 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ፥ አን​ተም በም​ድር ነህና በአ​ፍህ አት​ፍ​ጠን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቃልን ይና​ገር ዘንድ ልብህ አይ​ቸ​ኩል፤ ስለ​ዚ​ህም ቃልህ ጥቂት ይሁን።


ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ብሎ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነት፤ በጽ​ድ​ቅም ቢምል፥ አሕ​ዛብ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካሉ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።


ኤር​ም​ያ​ስም የአ​ኪ​ቃም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ ወደ አለ​በት ወደ መሴፋ ሄደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር በሀ​ገሩ ውስጥ በቀ​ሩት ሕዝብ መካ​ከል ተቀ​መጠ።


“የመንግሥቴ እኩሌታ ስንኳ ቢሆን የምትለምኚውን ሁሉ እሰጥሻለሁ፤” ብሎ ማለላት።


በነ​ጋም ጊዜ አይ​ሁድ ተሰ​ብ​ስ​በው፥ ጳው​ሎ​ስን እስ​ኪ​ገ​ድ​ሉት ድረስ እን​ዳ​ይ​በ​ሉና እን​ዳ​ይ​ጠጡ ተስ​ማ​ም​ተው ተማ​ማሉ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ቀኑ ምስ​ክ​ራ​ቸው እኔ ነኝና፤ ነገር ግን ዐው​ቀው አይ​ደ​ለም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ፥ ከገ​ለ​ዓ​ድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ።


በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ስላ​ደ​ረ​ጉት ስን​ፍና ሁሉ የብ​ን​ያም ገባ​ዖ​ንን ይወጉ ዘንድ ለሚ​ሄዱ ሕዝብ በመ​ን​ገድ ስንቅ የሚ​ይዙ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ከመ​ቶው ዐሥር ሰው፥ ከሺ​ሁም መቶ ሰው፥ ከዐ​ሥ​ሩም ሺህ አንድ ሺህ ሰው እን​ወ​ስ​ዳ​ለን።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች በብ​ን​ያም ልጆች ላይ ዳግ​መኛ ተመ​ለሱ፤ ሞላ​ውን ከተማ፥ ከብ​ቱ​ንም፥ ያገ​ኙ​ት​ንም ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት አጠፉ፤ ያገ​ኙ​ት​ንም ከተማ ሁሉ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ እንደ አንድ ሰው ተነ​ሥ​ተው እን​ዲህ አሉ፥ “ከእኛ ዘንድ ማንም ወደ ሀገሩ አይ​ሄ​ድም፤ ወደ ቤቱም አይ​መ​ለ​ስም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ “ልጁን ለብ​ን​ያም የሚ​ሰጥ ርጉም ይሁን ብለው ምለ​ዋ​ልና እኛ ከል​ጆ​ቻ​ችን ሚስ​ቶ​ችን ለእ​ነ​ርሱ መስ​ጠት አን​ች​ልም” አሉ።


አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሊጣ​ሉ​አ​ችሁ ወደ እኛ በመጡ ጊዜ፦ ስለ እኛ ማሩ​አ​ቸው፥ እኛ ሚስት ለያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በሰ​ልፍ አል​ወ​ሰ​ድ​ን​ላ​ቸ​ው​ምና፥ እና​ን​ተም በደል ይሆ​ን​ባ​ችሁ ስለ ነበር አላ​ጋ​ባ​ች​ኋ​ቸ​ው​ምና፥” እን​ላ​ቸ​ዋ​ለን።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ ስላ​ል​ወጣ ሰው፥ “እርሱ ፈጽሞ ይገ​ደል” ብለው ታላቅ መሐላ ምለው ነበ​ርና፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ወደ ጉባኤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያል​ወጣ ማን ነው?” አሉ።


እኛ ልጆ​ቻ​ች​ንን እን​ዳ​ን​ድ​ር​ላ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምለ​ና​ልና የተ​ረ​ፉት ሚስ​ቶ​ችን እን​ዲ​ያ​ገኙ ምን እን​ድ​ርግ?”


ሳኦ​ልም በዚያ ቀን ትልቅ በደል ፈጸመ፤ “ጠላ​ቶቼን እስ​ክ​በ​ቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚ​በላ ሰው ርጉም ይሁን” ብሎ ሕዝ​ቡን አም​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና። ሕዝ​ቡም ሁሉ እህል አል​ቀ​መ​ሱም። ሀገ​ሩም ሁሉ ምሳ አል​በ​ላም።