መሳፍንት 20:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብንያምም ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰው ሞተ፤ እነዚህም ሁሉ ጽኑዓን ሰዎች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጦርነቱም ላይ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ብንያማውያን ወደቁ፤ ሁሉም ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጦርነቱም ላይ ዐሥራ ስምንት ሺህ ብንያማውያን ወደቁ፤ ሁሉም ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብንያማውያን ምርጥ ወታደሮች ዐሥራ ስምንት ሺህ ተገደሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብንያምም አሥራ ስምንት ሺህ ሰው ሞተ፥ እነዚህ ሁሉ ጽኑዓን ነበሩ። |
እግዚአብሔርም ብንያምን በእስራኤል ፊት ጣላቸው፤ በዚያም ቀን የእስራኤል ልጆች ከብንያም ሃያ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሰዎችን ገደሉ፤ እነዚህም ሁሉ ሰይፍ የሚመዝዙ ነበሩ።
ከእነርሱም የተረፉት ተመልሰው ወደ ምድረ በዳ ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፤ ከእነርሱም በየመንገዱ ላይ አምስት ሺህ ሰውን ለቀሙ፤ ወደ ጊድዓምም አሳደዱአቸው፤ ከእነርሱም ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደሉ።