መሳፍንት 20:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ተመለሱ፤ የብንያምም ሰዎች ተሸበሩ፤ ክፉ ነገር እንደ ደረሰባቸውም አዩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እስራኤላውያን ዞረው አጠቋቸው፤ በዚህ ጊዜ ብንያማውያን ጥፋት እንደ ደረሰባቸው ስላወቁ እጅግ ደነገጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም እስራኤላውያን ዞረው አጠቋቸው፤ በዚህ ጊዜ ብንያማውያን ጥፋት እንደ ደረሰባቸው ስላወቁ እጅግ ደነገጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያንም የመልሶ ማጥቃት እርምጃቸውን በወሰዱ ጊዜ፥ ጨርሰው መደምሰሳቸውን ስለ ተገነዘቡ ብንያማውያን በፍርሃት ተሸበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ሰዎች ተመለሱ፥ የብንያምም ሰዎች ክፉ ነገር እንደ ደረሰባቸው አይተዋልና ደነገጡ። |
በጽዮን ያሉ ኀጢአተኞች ፈሩ፤ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎችን ያዘ፤ እሳት እንደሚነድድ የሚነግራችሁ ማን ነው? የዘለዓለም ሀገርንስ የሚነግራችሁ ማን ነው?
የጋይም ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው በተመለከቱ ጊዜ የከተማዪቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወዲህና ወዲያ መሸሽ አልቻሉም፤ ወደ ምድረ በዳም የሸሹ ሕዝብ በሚያሳድዱአቸው ላይ ተመለሱ።
እነዚህ ግን ለመጠመድና ለመጥፋት በፍጥረታቸው እንደ ተወለዱ አእምሮ እንደ ሌላቸው እንስሶች ሆነው፥ በማያውቁት ነገር እየተሳደቡ በጥፋታቸው ይጠፋሉ፤