መሳፍንት 20:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእስራኤልም ሁሉ የተመረጡ ዐሥር ሺህ ሰዎች ወደ ገባዖን አንጻር መጡ፤ ውጊያውም በርትቶ ነበር፤ መከራም እንዲያገኛቸው አላወቁም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከመላው እስራኤል የተውጣጣው ዐሥር ሺሕ ጦር በጊብዓ ላይ ፊት ለፊት አደጋ ጣለ። ውጊያው ከመበርታቱ የተነሣም፣ ብንያማውያን መጥፊያቸው እየቀረበ መምጣቱን ገና አላወቁም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ከመላው እስራኤል የተውጣጣው ዐሥር ሺህ ጦር በጊብዓ ላይ ፊት ለፊት አደጋ ጣለ። ውጊያው ከመበርታቱ የተነሣም፥ ብንያማውያን መጥፊያቸው እየቀረበ መምጣቱን ገና አላወቁም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእስራኤል በልዩ ሁኔታ የተመረጡት ዐሥር ሺህ ሰዎች በጊብዓ ላይ አደጋ ጣሉ፤ ውጊያውም ከባድ ሆነ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ብንያማውያን በቅርብ ጊዜ ችግር እንደሚደርስባቸው አልተገነዘቡም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤልም ሁሉ የተመረጡ አሥር ሺህ ሰዎች ወደ ጊብዓ አንጻር መጡ፥ ሰልፍም በርትቶ ነበር፥ መከራም እንዲያገኛቸው አላወቁም ነበር። |
ሰውም ጊዜውን አያውቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች ፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።
ስለዚህ ምክንያት ጥፋት ይመጣብሻል፤ ጥልቀቱን አታውቂም፤ በውስጡም ትወድቂያለሽ፤ ጕስቁልና ይመጣብሻል፤ ማምለጥም አይቻልሽም፤ ሞት ድንገት ይመጣብሻል፤ አታውቂምም።
“ራሳችሁን ጠብቁ፤ በመብልና በመጠጥ፥ በመቀማጠልና የዓለምን ኑሮ በማሰብ ልባችሁን አታደንድኑ፤ ያቺ ቀንም በድንገት ትደርስባችኋለች።
የጋይም ንጉሥ በሰማ ጊዜ ፈጥኖ ሄደ። የከተማዪቱም ሰዎች ወጡ፤ እርሱና ሕዝቡም ሁሉ በተወሰነው ጊዜ በዓረባ ፊት ባለው አንድ ስፍራ እስራኤልን በጦርነት ተቀበሉአቸው፤ እርሱ ግን ከከተማዪቱ በስተኋላ እንደ ተደበቁ አያውቅም ነበር።
እግዚአብሔርም ብንያምን በእስራኤል ፊት ጣላቸው፤ በዚያም ቀን የእስራኤል ልጆች ከብንያም ሃያ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሰዎችን ገደሉ፤ እነዚህም ሁሉ ሰይፍ የሚመዝዙ ነበሩ።