ዳዊትም እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “በኋላቸው ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ አትውጣ።
መሳፍንት 20:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ገባዖንን የሚከብቡአት ሰዎችን በዙሪያዋ አኖሩባት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እስራኤላውያን በጊብዓ ዙሪያ ድብቅ ጦር አኖሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም እስራኤላውያን በጊብዓ ዙሪያ ድብቅ ጦር አኖሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እስራኤላውያን ጥቂት ወታደሮችን በጊብዓ ዙሪያ እንዲሸምቁ አደረጉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም በጊብዓ ዙሪያ የተደበቁ ሰዎች አኖሩባት። |
ዳዊትም እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “በኋላቸው ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ አትውጣ።
በኢያሪኮና በንጉሥዋም እንዳደረግህ እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ ታደርጋለህ፤ የከብቱን ምርኮ ግን ለራሳችሁ ትዘርፋላችሁ፤ ከከተማዪቱም በስተኋላ ይከብቧት ዘንድ ጦር ላክ” አለው።
እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፥ “እነሆ፥ ሂዱና ከከተማዪቱ በስተኋላ ተደበቁ፤ ከከተማዪቱ አትራቁ፤ ሁላችሁም ተዘጋጅታችሁ ተቀመጡ፤
ከእስራኤልም ሁሉ የተመረጡ ዐሥር ሺህ ሰዎች ወደ ገባዖን አንጻር መጡ፤ ውጊያውም በርትቶ ነበር፤ መከራም እንዲያገኛቸው አላወቁም ነበር።