የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ከብንያም ጋር ሊዋጉ ወጡ፤ በገባዖንም ገጠሙአቸው።
የእስራኤል ሰዎች ብንያማውያንን ለመውጋት ሄዱ፤ በጊብዓ ለሚያደርጉትም ውጊያ ቦታ ቦታቸውን ያዙ።
በብንያም ሠራዊት ላይ አደጋ ለመጣል ሄዱ፤ ወታደሮቻቸውንም በጊብዓ ትይዩ አሰለፉ፤
የእስራኤልም ሰዎች ከብንያም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ የእስራኤልም ሰዎች በጊብዓ አጠገብ በእነርሱ ላይ ተሰልፈው ቆሙ።
የእስራኤልም ልጆች በማለዳ ተነሥተው በገባዖን ፊት ሰፈሩ።
የብንያምም ልጆች ከገባዖን ወጡ፤ በዚያም ቀን ከእስራኤላውያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎችን በምድር ላይ ገደሉ።