መሳፍንት 20:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች በማለዳ ተነሥተው በገባዖን ፊት ሰፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ጧት እስራኤላውያን ተነሥተው በጊብዓ አጠገብ ሰፈሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግሥቱ ጧት እስራኤላዋያን ነሥተው በጊብዓ አጠገብ ሰፈሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በማግስቱ ጧት ጒዞ ጀመሩ፤ በጊብዓ አጠገብም ሰፈሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች በማለዳ ተነሥተው በጊብዓ ፊት ሰፈሩ። |
የእስራኤልም ልጆች ተነሥተው ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርንም፥ “የብንያምን ልጆች ለመውጋት መሪ ሆኖ ማን ይውጣልን?” ብለው ጠየቁት፤ እግዚአብሔርም፥ “ይሁዳ መሪ ይሁን” አለ፤