La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 20:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ስላ​ደ​ረ​ጉት ስን​ፍና ሁሉ የብ​ን​ያም ገባ​ዖ​ንን ይወጉ ዘንድ ለሚ​ሄዱ ሕዝብ በመ​ን​ገድ ስንቅ የሚ​ይዙ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ከመ​ቶው ዐሥር ሰው፥ ከሺ​ሁም መቶ ሰው፥ ከዐ​ሥ​ሩም ሺህ አንድ ሺህ ሰው እን​ወ​ስ​ዳ​ለን።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከመላው የእስራኤል ነገዶችም ለሰራዊቱ ስንቅ እንዲይዙ፣ ከመቶው ዐሥር፣ ከሺው አንድ መቶ፣ ከዐሥር ሺሑ ደግሞ አንድ ሺሕ ሰው እንወስዳለን። ከዚያም ሰራዊቱ በብንያም ወደምትገኘው ጌባዕ በሚደርስበት ጊዜ፣ ነዋሪዎቿ በእስራኤል ላይ ለፈጸሙት አስነዋሪ ድርጊት ተገቢውን ቅጣት ይሰጣቸዋል።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከመላው የእስራኤል ነገዶችም ለሠራዊቱ ስንቅ እንዲይዙ፥ ከመቶው ዐሥር፥ ከሺው አንድ መቶ፥ ከዐሥር ሺው ደግሞ አንድ ሺህ ሰው እንወስዳለን። ከዚያም ሠራዊቱ በብንያም ወደምትገኘው ጊብዓ በሚደርስበት ጊዜ፥ ነዋሪዎችዋ በእስራኤል ላይ ለፈጸሙት አስነዋሪ ድርጊት ተገቢውን ቅጣት ይሰጣቸዋል።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በእስራኤል ላይ በፈጸሙት አሳፋሪ ተግባር በብንያም ግዛት የምትገኘውን የጊብዓን ሕዝብ ለመበቀል ለሚዘምተው ሠራዊት ስንቅ ያቀብሉ ዘንድ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ከመቶ ዐሥር፥ ከሺህ መቶ፥ ከዐሥር ሺህ አንድ ሺህ ሰው እንመድባለን።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ብንያም ጊብዓ በመጡ ጊዜ እርስዋ በእስራኤል ላይ እንዳደረገችው እንደ ስንፍናዋ እንዲያደርጉ፥ ለሕዝብ ስንቅ የሚይዙ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ከመቶው አሥር ሰው ከሺሁም መቶ ሰው ከአሥሩም ሺህ አንድ ሺህ ሰው እንወስዳለን።

Ver Capítulo



መሳፍንት 20:10
7 Referencias Cruzadas  

“ከፊ​ታ​ችሁ የማ​ሳ​ድ​ዳ​ቸው አሕ​ዛብ በእ​ነ​ዚህ ሁሉ ረክ​ሰ​ዋ​ልና በእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች ሁሉ አት​ር​ከሱ።


ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያው​ጡ​አት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ስን​ፍ​ናን አድ​ር​ጋ​ለ​ችና፥ የአ​ባ​ቷ​ንም ቤት አስ​ነ​ው​ራ​ለ​ችና የከ​ተ​ማው ሰዎች በድ​ን​ጋይ ወግ​ረው ይግ​ደ​ሉ​አት፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ልህ ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።


ምል​ክት የታ​የ​በት ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን አፍ​ር​ሶ​አ​ልና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ በደል አድ​ር​ጎ​አ​ልና፥ እር​ሱና ያለው ሁሉ በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላሉ።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ላይ ተሰ​በ​ሰቡ።


እኔም ዕቅ​ብ​ቴን ይዤ በመ​ለ​ያ​ያዋ ቈራ​ረ​ጥ​ኋት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ እን​ደ​ዚህ ያለ ስን​ፍና ስለ ሠሩ ወደ እስ​ራ​ኤል ርስት አው​ራጃ ሁሉ ሰደ​ድሁ።


አሁ​ንም በገ​ባ​ዖን ላይ እን​ዲህ አድ​ርጉ፤ በየ​ዕ​ጣ​ችን እን​ዘ​ም​ት​ባ​ቸ​ዋ​ለን።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች፥ “ከእኛ ማንም ሰው ሴት ልጁን ለብ​ን​ያም ልጆች በጋ​ብቻ አይ​ስጥ” ብለው በመ​ሴፋ ተማ​ማሉ።