መሳፍንት 19:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአምስተኛውም ቀን ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፤ የብላቴናዪቱም አባት፥ “እህል ብላ፤ ከዚህም በኋላ ፀሐይ ሲበርድ ትሄዳለህ” አለው። ሁለቱም በሉ፤ ጠጡም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐምስተኛውም ቀን ጧት ሌዋዊው ለመሄድ ሲነሣ፣ የልጅቱ አባት “ሰውነትህን አበርታ፤ ጥላው እስኪበርድም ድረስ በዚሁ ቈይ” አለው፤ ስለዚህ ሁለቱም ዐብረው በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአምስተኛውም ቀን ጠዋት ሌዋዊው ለመሄድ ሲነሣ፥ የልጂቱ አባት “ሰውነትህን አበርታ፤ ጥላው እስኪበርድም ድረስ በዚሁ ቈይ” አለው፤ ስለዚህ ሁለቱም አብረው በሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአምስተኛው ቀን ጧት በማለዳ ተነሥቶ ጒዞ ጀመረ፤ የልጅቱ አባት ግን “እባክህ እህል ቅመስ፤ ቈየት ብለህ ትሄዳለህ” አለው፤ ስለዚህም ሁለቱ ሰዎች አብረው በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአምስተኛውም ቀን ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፥ የብላቴናይቱም አባት፦ እባክህ፥ ሰውነትህን አበርታ፥ ቀኑም እስኪዋገድ ድረስ ቆይ አለው። ሁለቱም በሉ። |
በአራተኛውም ቀን ማልደው ተነሡ፤ እርሱም ለመሄድ ተነሣ፤ የብላቴናዪቱም አባት አማቹን፥ “ሰውነትህን በቁራሽ እንጀራ አበርታ፤ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ” አለው።
ሰውዬውም ከዕቅብቱና ከብላቴናው ጋር ለመሄድ ተነሣ፤ የብላቴናዪቱ አባት አማቱም፥ “እነሆ፥ መሽትዋል፤ ፀሐዩም ሊጠልቅ ደርሷል፤ ዛሬም እዚህ እደር፤ በዚህም ተቀመጥ፤ ልብህም ደስ ይበለው፤ በጥዋትም መንገዳችሁን ትገሠግሣላችሁ፤ ወደ ቤትህም ትገባለህ” አለው።