ከዛፉም ሥር ዕረፉ፤ እንጀራም እናምጣላችሁና ብሉ፤ ከዚያም በባሪያችሁ ዘንድ ከአረፋችሁ በኋላ፥ ወደ ዐሰባችሁት ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፥ “እንዳልህ እንዲሁ አድርግ” አሉት።
መሳፍንት 19:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአራተኛውም ቀን ማልደው ተነሡ፤ እርሱም ለመሄድ ተነሣ፤ የብላቴናዪቱም አባት አማቹን፥ “ሰውነትህን በቁራሽ እንጀራ አበርታ፤ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአራተኛው ቀን ማልደው ተነሡ፤ እንግዳውም ለመሄድ ተዘጋጀ፤ የልጅቱ አባት ግን፣ “እንድትበረታ እህል ቅመስ፤ ከዚያም መሄድ ትችላለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአራተኛው ቀን ማልደው ተነሡ፤ እንግዳውም ለመሄድ ተዘጋጀ፤ የልጂቱ አባት ግን፥ “እንድትበረታ እህል ቅመስ፤ ከዚያም መሄድ ትችላለህ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአራተኛው ቀን ጧት በማለዳ ተነሡና ለመሄድ ተዘጋጁ፤ የልጅቱ አባት ግን የልጁን ባል “ብርታት እንድታገኝ መጀመሪያ እህል ቅመስ፤ ከዚያም በኋላ ትሄዳለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአራተኛውም ቀን ማልደው ተነሡ፥ እርሱም ለመሄድ ተነሣ፥ የብላቴናይቱም አባት አማቹን፦ ሰውነትህን በቁራሽ እንጀራ አበርታ፥ ከዚያም በኋላ ትሄዳለህ አለው። |
ከዛፉም ሥር ዕረፉ፤ እንጀራም እናምጣላችሁና ብሉ፤ ከዚያም በባሪያችሁ ዘንድ ከአረፋችሁ በኋላ፥ ወደ ዐሰባችሁት ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፥ “እንዳልህ እንዲሁ አድርግ” አሉት።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የእኔስ መብል የላከኝን የአባቴን ፈቃድ አደርግ ዘንድ፥ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።
በአምስተኛውም ቀን ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፤ የብላቴናዪቱም አባት፥ “እህል ብላ፤ ከዚህም በኋላ ፀሐይ ሲበርድ ትሄዳለህ” አለው። ሁለቱም በሉ፤ ጠጡም።
ከበለሱም ጥፍጥፍ ቍራጭ ሰጡትና በላ፤ ነፍሱም ወደ እርሱ ተመለሰች፤ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንጀራ አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም ነበርና።