La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 19:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከዚ​ያም በኋላ ያያት ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዲህ ያለ ነገር የሆ​ነ​በት ጊዜ የለም፤ የታ​የ​በ​ትም ጊዜ የለም፤” ያም ሰው እነ​ዚ​ያን የላ​ካ​ቸ​ውን ሰዎች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች እን​ዲህ በሏ​ቸው፦ እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ ከወጡ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ እን​ዲህ የሆ​ነ​በት ጊዜ አለን? እና​ንተ ተመ​ካ​ከ​ሩ​በት፤ የሚ​በ​ጀ​ው​ንም ተነ​ጋ​ገሩ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ያየም ሁሉ፣ “እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ ጀምሮ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልታየም፤ አልተደረገም፤ ምን ማድረግ እንዳለብንም በነገሩ አስቡበት፤ ተመካከሩበት” ተባባሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ያየም ሁሉ፥ “እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ ጀምሮ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልታየም፤ አልተደረገም፤ ምን ማድረግ እንዳለብንም በነገሩ አስቡበት፤ ተመካከሩ በት” ተባባሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያ በኋላ የላካቸውን ሰዎች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ለእስራኤላውያን ሁሉ እንዲህ በሉአቸው፦ ‘የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ተደርጎ ያውቃልን? አስቡበት፤ ተመካከሩበት ተነጋገሩበትም።’ ” ያዩት ሁሉ “እስከዚህ ጊዜ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ታይቶም አይታወቅ!” አሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ያየም ሁሉ፦ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልተደረገም፥ አልታየምም፥ አስቡት፥ በዚህም ተመካከሩ፥ ተነጋገሩም ይባባል ነበር።

Ver Capítulo



መሳፍንት 19:30
7 Referencias Cruzadas  

መምህር የሌላቸው እንደ ቅጠል ይወድቃሉ። በምክር ብዛት ግን ደኅንነት ይኖራል።


ክፉ ሰው ከመሳደብ ጋር ክፋትን ይሠራል፤ ራሳቸውን የሚያውቁ ግን ብልሆች ናቸው።


ማኅበርን የሚያከብሩ ማስተዋልን ገንዘብ ያደርጋሉ። ምክርም በመካሮች ልብ ትኖራለች።


ዐሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ።


በአስተዳደር ጦርነት ይደረጋል፤ ርዳታም ከምትመክር ልብ ጋር ይሆናል።


በጊ​ብዓ ዘመን እንደ ነበረ እጅግ ረከሱ፤ እር​ሱም በደ​ላ​ቸ​ውን ያስ​ባል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይበ​ቀ​ላል።


እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ ሁላ​ችሁ፥ ምክ​ራ​ች​ሁ​ንና እዝ​ና​ታ​ች​ሁን በዚህ ስጡ።”