እነሆ፥ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁ፤ እንደ ወደዳችሁም አድርጉአቸው፤ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም በደል አታድርጉ፤ እነርሱ በቤቴ ጥላ ሥር ገብተዋልና።”
መሳፍንት 19:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባለቤቱም ሽማግሌው ወደ እነርሱ ወጥቶ፥ “ወንድሞቼ ሆይ! ይህን ክፉ ነገር ታደርጉ ዘንድ አይገባችሁም፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ከገባ በኋላ እንደዚህ ያለ ስንፍና አትሥሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤቱም ባለቤት ወደ ውጭ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “የለም ወዳጆቼ፤ እንዲህ አትሁኑ፤ ሰውየው እንግዳዬ ስለ ሆነ ይህን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቤቱም ባለቤት ወደ ውጭ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “የለም ወዳጆቼ፤ እንዲህ አትሁኑ፤ ሰውየው እንግዳዬ ስለ ሆነ ይህን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሽማግሌው ግን ወደ ውጪ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “አይሆንም ወዳጆቼ ሆይ! እባካችሁ ይህን የመሰለ አስከፊ ነገር አታድርጉ! ይህ ሰው የእኔ እንግዳ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባለቤቱም ሽማግሌው ወደ እነርሱ ወጥቶ፦ ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር፥ እባካችሁ፥ አታድርጉ፥ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ገብቶአልና እንደዚህ ያለ ኃጢአት አትሥሩ። |
እነሆ፥ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁ፤ እንደ ወደዳችሁም አድርጉአቸው፤ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም በደል አታድርጉ፤ እነርሱ በቤቴ ጥላ ሥር ገብተዋልና።”
የያዕቆብም ልጆች ከምድረ በዳ መጡ፤ ይህንም በሰሙ ጊዜ ፈጽመው ደነገጡ፤ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፤ እጅግም ተቈጡ፤ እንዲህ አይደረግምና።
እርስዋም አለችው፥ “ወንድሜ ሆይ፥ አታዋርደኝ፤ እንዲህ ያለ ነገር በእስራኤል ዘንድ አይገባምና ይህን ነውረኛ ሥራ አታድርግ።
ብላቴናዪቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያውጡአት፤ በእስራኤልም ዘንድ ስንፍናን አድርጋለችና፥ የአባቷንም ቤት አስነውራለችና የከተማው ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉአት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።
ምልክት የታየበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል አድርጎአልና፥ እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ።”
እኔም ዕቅብቴን ይዤ በመለያያዋ ቈራረጥኋት፤ በእስራኤልም ዘንድ እንደዚህ ያለ ስንፍና ስለ ሠሩ ወደ እስራኤል ርስት አውራጃ ሁሉ ሰደድሁ።