La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 19:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዐይ​ኑ​ንም አን​ሥቶ መን​ገ​ደ​ኛ​ውን በከ​ተ​ማው አደ​ባ​ባይ አየ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ውም፥ “ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ? ከወ​ዴ​ትስ መጣህ?” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሽማግሌው ቀና ብሎ መንገደኛውን በከተማዪቱ አደባባይ ላይ ባየው ጊዜ፣ “ከወዴት መጣህ? ወዴትስ ትሄዳለህ?” ሲል ጠየቀው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሽማግሌው ቀና ብሎ መንገደኛውን በከተማይቱ አደባባይ ላይ ባየው ጊዜ፥ “ከወዴት መጣህ? ወዴትስ ትሄዳለህ?” ሲል ጠየቀው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሽማግሌውም በከተማይቱ አደባባይ የተቀመጠውን ሰው አይቶ “ከየት መጣህ? የምትሄደውስ ወዴት ነው?” ሲል ጠየቀው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዓይኑንም አንሥቶ መንገደኛውን በከተማው አደባባይ አየ፥ ሽማግሌውም፦ ወዴት ትሄዳለህ? ከወዴትስ መጣህ? አለው።

Ver Capítulo



መሳፍንት 19:17
7 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “የሦራ አገ​ል​ጋይ አጋር ሆይ፥ ከወ​ዴት መጣሽ? ወዴ​ትስ ትሄ​ጂ​ያ​ለሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “እኔ ከእ​መ​ቤቴ ከሦራ ፊት እኰ​በ​ል​ላ​ለሁ” አለች።


የፊ​ተ​ኛ​ው​ንም እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “ወን​ድሜ ዔሳው ያገ​ኘህ እንደ ሆነ፦ ‘አንተ የማን ነህ? ወዴ​ትስ ትሄ​ዳ​ለሀ? በፊ​ትህ ያለው ይህስ መንጋ የማን ነው?’ ብሎ የጠ​የ​ቀ​ህም እን​ደ​ሆነ፥


ወደ ባለ​ጠ​ጋ​ውም እን​ግዳ በመጣ ጊዜ ከበ​ጉና ከላሙ ወስዶ ለዚያ ወደ እርሱ ለመ​ጣው እን​ግዳ ያዘ​ጋ​ጅ​ለት ዘንድ ሳሳ፤ የዚ​ያ​ንም የድ​ሃ​ውን ሰው በግ ወስዶ ለዚያ ለመ​ጣው ሰው አዘ​ጋጀ።


መን​ገ​ዶች ባድማ ሆኑ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብም መፈ​ራት ቀረ፤ ቃል ኪዳ​ና​ቸ​ውም ፈረሰ፤ እንደ ሰውም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ታ​ቸ​ውም።


ጌታ ሆይ! አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ተስፋ ነህ፤ በመ​ከ​ራም ጊዜ ታድ​ነ​ዋ​ለህ፤ በም​ድር እንደ እን​ግዳ፥ ወደ ማደ​ሪ​ያም ዘወር እን​ደ​ሚል መን​ገ​ደኛ ስለ ምን ትሆ​ና​ለህ?


እነ​ሆም አንድ ሽማ​ግሌ ከእ​ር​ሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፤ ይህም ሰው ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር ነበረ፤ በገ​ባ​ዖ​ንም በእ​ን​ግ​ድ​ነት ተቀ​ምጦ ነበር፤ የዚያ ሀገር ሰዎች ግን የብ​ን​ያም ልጆች ነበሩ።


እር​ሱም፥ “እኛ ከይ​ሁዳ ቤተ ልሔም ወደ ተራ​ራ​ማው ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ማዶ እና​ል​ፋ​ለን፤ እኔ ከዚያ ነኝ፤ ወደ ይሁዳ ቤተ ልሔ​ምም ሄጄ ነበር፥ አሁ​ንም ወደ ቤቴ እሄ​ዳ​ለሁ፤ በቤ​ቱም የሚ​ያ​ሳ​ድ​ረኝ አጣሁ፤