ሦስት ዓመትም በኢየሩሳሌም ነገሠ፤ የእናቱም ስም መዓካ ነበረ፤ የገባዖን ሰው የኡርኤል ልጅ ነበረች። በአብያና በኢዮርብዓም መካከልም ሰልፍ ነበረ።
መሳፍንት 19:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አልፈውም ሄዱ፤ የብንያምም ነገድ በምትሆነው በገባዖን አጠገብ ሳሉ ፀሐይ ገባችባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም መንገዳቸውን ቀጠሉ፤ የብንያም ነገድ ወደሆነችው ወደ ጊብዓ እንደ ደረሱም ፀሓይ ጠለቀች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም መንገዳቸውን ቀጠሉ፤ የብንያም ነገድ ወደ ሆነችው ወደ ጊብዓ እንደ ደረሱም ፀሓይ ጠለቀች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ኢየሩሳሌምን አልፈው ጒዞአቸውን ወደፊት ቀጠሉ፤ በብንያም ግዛት በምትገኘው በጊብዓ ሲደርሱ ፀሐይ ጠለቀች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዳቸውንም ይዘው ሄዱ፥ የብንያምም ነገድ በምትሆነው በጊብዓ አጠገብ ሳሉ ፀሐይ ገባችባቸው። |
ሦስት ዓመትም በኢየሩሳሌም ነገሠ፤ የእናቱም ስም መዓካ ነበረ፤ የገባዖን ሰው የኡርኤል ልጅ ነበረች። በአብያና በኢዮርብዓም መካከልም ሰልፍ ነበረ።
በገባዖንም ገብተው ያድሩ ዘንድ ወደዚያ አቀኑ። ገብተውም በከተማው አደባባይ በተቀመጡ ጊዜ ወደ ቤቱ የሚያስገባቸውና የሚያሳድራቸው አልነበረም።
እነሆም አንድ ሽማግሌ ከእርሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፤ ይህም ሰው ከተራራማው ከኤፍሬም ሀገር ነበረ፤ በገባዖንም በእንግድነት ተቀምጦ ነበር፤ የዚያ ሀገር ሰዎች ግን የብንያም ልጆች ነበሩ።