መሳፍንት 19:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናውንም፥ “ና፤ ከእነዚህ ስፍራ ወደ አንዱ እንቅረብ፤ በገባዖን ወይም በራማ እንደር” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም፣ “በል ና፤ ወደ ጊብዓ ወይም ወደ ራማ ለመድረስ እንሞክርና ከዚያ በአንዱ ስፍራ እናድራለን” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀጥሎም፥ “በል ና፤ ወደ ጊብዓ ወይም ወደ ራማ ለመድረስ እንሞክርና ከዚያ በአንዱ ስፍራ እናድራለን” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሽከሩንም “ና ከእነዚህ ቦታዎች ወደ አንዱ እንቅረብ፤ በጊብዓ ወይም በራማ እንደር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሽከሩንም፦ ና፥ ከእነዚህ ስፍራ ወደ አንዱ እንቅረብ፥ በጊብዓ ወይም በራማ እንደር አለው። |
ኢየሩሳሌም የምትባል የኢያቡሴዎን ከተማና የኢያሪሞን ከተማ ገባዖን፤ ዐሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።