La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በኢ​ያ​ቡ​ስም አን​ጻር ገና ሳሉ ፀሐ​ይዋ ተቈ​ለ​ቈ​ለች፤ ብላ​ቴ​ና​ውም ጌታ​ውን፥ “ና፤ ወደ​ዚ​ህች ወደ ኢያ​ቡ​ሳ​ው​ያን ከተማ፥ እባ​ክህ እና​ቅና፤ በእ​ር​ስ​ዋም እን​ደር” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደ ኢያቡስ እንደ ቀረቡም ጊዜው እየመሸ ስለ ነበር አገልጋዩ ጌታውን፣ “እንግዲህ ወደዚህች ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ ጐራ ብለን እንደር” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ የቡስ እንደ ቀረቡም ጊዜው እየመሸ ስለ ነበር አገልጋዩ ጌታውን፥ “እንግዲህ ወደዚህች ወደ የቡሳውያን ከተማ ጐራ ብለን እንደር” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወደ ኢያቡስ በደረሱ ጊዜ መሸባቸው፤ አሽከሩም ጌታውን “ና እባክህ ወደ እዚህ ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ እንመለስና እዚያ እንደር” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ኢያቡስም በደረሱ ጊዜ መሸባቸው፥ አሽከሩም ጌታውን፦ ና፥ ወደዚህ ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ፥ እባክህ፥ እናቅና፥ በእርስዋም እንደር አለው።

Ver Capítulo



መሳፍንት 19:11
8 Referencias Cruzadas  

ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ንን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ንን፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ንን፥


ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በሀ​ገሩ ውስጥ ወደ​ሚ​ኖ​ሩት ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሄዱ፤ እነ​ር​ሱም ዳዊ​ትን፥ “ወደ​ዚህ አት​ገ​ባም” አሉት። ዕው​ሮ​ችና አን​ካ​ሶ​ችም ወደ​ዚህ አት​ገ​ባም ብለው ተቃ​ወ​ሙት።


ኤያ​ቡ​ሴ​ዎ​ንን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ንን፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ንን፥


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ግን የይ​ሁዳ ልጆች ሊያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ቸው አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም፤ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም እስከ ዛሬ ድረስ በይ​ሁዳ ልጆች መካ​ከል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል።


ነገር ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን የብ​ን​ያም ልጆች አላ​ወ​ጡ​አ​ቸ​ውም፤ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር እስከ ዛሬ ድረስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​ም​ጠ​ዋል።


ሰው​ዬው ግን በዚያ ሌሊት ለማ​ደር አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወደ ተባ​ለ​ችው ወደ ኢያ​ቡስ ፊት ለፊት ደረሰ። ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት የተ​ጫኑ አህ​ዮች ነበሩ፤ ዕቅ​ብ​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ረች።


ጌታ​ውም፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወዳ​ል​ሆ​ነች ወደ እን​ግዳ ከተማ አን​ገ​ባም፤ እኛ ወደ ገባ​ዖን እን​ለፍ” አለው።


ለአ​ህ​ዮ​ቻ​ችን ገለ​ባና ገፈራ አለን፤ ለእ​ኔና ለገ​ረ​ድህ ከባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህም ጋር ላለው ብላ​ቴና እን​ጀ​ራና የወ​ይን ጠጅ አለን፤ ከሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገን ሁሉ አን​ዳ​ችም አላ​ጣ​ንም” አለው።