መሳፍንት 18:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳንም ልጆች መንገዳቸውን ሄዱ፤ ሚካም ከእርሱ እንደ በረቱ ባየ ጊዜ ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ።። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳን ሰዎች ይህን ብለው መንገዳቸውን ቀጠሉ፤ ሚካም የማይችላቸው መሆኑን በማየት ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳን ሰዎች ይህን ብለው መንገዳቸውን ቀጠሉ፤ ሚካም የማይችላቸው መሆኑን በማየት ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ጒዞአቸውን ቀጠሉ፤ ሚካም ሊቋቋማቸው እንደማይችል ባየ ጊዜ ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳንም ልጆች መንገዳቸውን ሄዱ፥ ሚካም ከእርሱ እንደ በረቱ ባየ ጊዜ ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ። |
“የነገዶችም ስም ይህ ነው። በሔትሎን መንገድ አጠገብ ወደ ሐማት መግቢያ፥ በደማስቆም ድንበር በአለው በሐጸርዔናን በሐማትም አጠገብ በሰሜን በኩል ይጀምራል። ድንበራቸውም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል። ለዳን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
የዳንም ልጆች እንዲህ አሉት፥ “የተቈጡ ሰዎች እንዳያገኙህና ነፍስህም፥ የቤተ ሰቦችህም ነፍስ እንዳይጠፋብህ፥ ድምፅህ በእኛ መካከል አይሰማ።”
እነርሱም ሚካ የሠራውን ጣዖትና ለእርሱ የነበረውን ካህን ይዘው ወደ ሌሳ፥ ጸጥ ብሎ ተዘልሎም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ መጡ፤ በሰይፍም ስለት መቱአቸው፤ ከተማዪቱንም በእሳት አቃጠሉአት።