በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው በርስቱ ዳርቻ በተምናሴራ ቀበሩት። በዚያም ከግብፅ በወጡ ጊዜ እግዚአብሔር እንዳዘዘው የእስራኤልን ልጆች በገልገላ የገረዘባቸውን የድንጋይ ባልጩቶችን እርሱን በቀበሩበት መቃብር ከእርሱ ጋር ቀበሩ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።
መሳፍንት 18:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ወደ ተራራማው ወደ ኤፍሬም አገር አለፉ እስከ ሚካም ቤት ደረሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ተጕዘው ወደ ኰረብታማው የኤፍሬም አገር በመሄድ ወደ ሚካ ቤት መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ተጉዘው ወደ ኰረብታማው የኤፍሬም አገር በመሄድ ወደ ሚካ ቤት መጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ጒዞአቸውን በመቀጠል በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ወደሚገኘው ወደ ሚካ ቤት መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ወደ ተራራማው ወደ ኤፍሬም አገር አለፉ፥ ወደ ሚካም ቤት መጡ። |
በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው በርስቱ ዳርቻ በተምናሴራ ቀበሩት። በዚያም ከግብፅ በወጡ ጊዜ እግዚአብሔር እንዳዘዘው የእስራኤልን ልጆች በገልገላ የገረዘባቸውን የድንጋይ ባልጩቶችን እርሱን በቀበሩበት መቃብር ከእርሱ ጋር ቀበሩ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።
የአሮንም ልጅ ሊቀ ካህናቱ አልዓዛር ሞተ፤ በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር ለልጁ ለፊንሐስ በተሰጠችው በጊብዓት መሬት ቀበሩት።
ወጥተውም በይሁዳ ቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፤ ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር ተብሎ ተጠራ፤ እነሆም፥ ቦታዉ ከቂርያትይዓሪም በስተኋላ ነው።
የሌሳን ምድር ሊሰልሉ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎችም ወንድሞቻቸውን፥ “በእነዚህ ቤቶች ውስጥ ኢፉድና ተራፊም፥ የተቀረፀ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስልም እንዳሉ ታውቃላችሁን?፤ አሁንም የምታደርጉትን ዕወቁ” ብለው ተናገሩአቸው።
በዚያም ዘመን ለእስራኤል ንጉሥ አልነበራቸውም። በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር ማዶ የተቀመጠ አንድ ሌዋዊ ሰው ነበረ፤ ከይሁዳ ቤተ ልሔምም ዕቅብት አገባ።