መሳፍንት 18:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዳን ወገንም የጦር ዕቃ የታጠቁ ስድስት መቶ ሰዎች ከዚያ ከሶራሕና ከእስታሔል ተነሥተው ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ በኋላም ከዳን ወገን ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ስድስት መቶ ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ተነሡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ በኋላም ከዳን ወገን ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ስድስት መቶ ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ተነሡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ከዳን ነገድ የጦር መሣሪያ የታጠቁ ስድስት መቶ ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ተነሡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዳን ወገንም የጦር ዕቃ የታጠቁ ስድስት መቶ ሰዎች ከዚያ ከጾርዓና ከኤሽታኦል ተነሥተው ሄዱ። |
በሄዳችሁም ጊዜ ተዘልለው ወደ ተቀመጡ ሕዝብ ትደርሳላችሁ፤ ምድሪቱም ሰፊ ናት፤ እግዚአብሔርም በምድር ካለው ነገር ሁሉ አንዳች የማይጐድልባትን ስፍራ በእጃችሁ ሰጥቶአል” አሉ።
ወጥተውም በይሁዳ ቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፤ ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር ተብሎ ተጠራ፤ እነሆም፥ ቦታዉ ከቂርያትይዓሪም በስተኋላ ነው።