በሄዳችሁም ጊዜ ተዘልለው ወደ ተቀመጡ ሕዝብ ትደርሳላችሁ፤ ምድሪቱም ሰፊ ናት፤ እግዚአብሔርም በምድር ካለው ነገር ሁሉ አንዳች የማይጐድልባትን ስፍራ በእጃችሁ ሰጥቶአል” አሉ።
እዚያ ስትደርሱም በመተማመን የሚኖር ሕዝብ፣ እግዚአብሔር በእጃችሁ የሚሰጣችሁን አንዳች ነገር ያልጐደላትን ሰፊ ምድር ታገኛላችሁ።”
እዚያ ስትደርሱም ያለ ሥጋት የሚኖር ሕዝብ፥ እግዚአብሔር በእጃችሁ የሚሰጣችሁን አንዳች ነገር ያልጐደላትን ሰፊ ምድር ታገኛላችሁ።”
ወደዚያም በምትሄዱበት ጊዜ ምንም የማይጠራጠሩ ሰላም ወዳዶች ሆነው ታገኙአቸዋላችሁ፤ አገሪቱ ታላቅ ናት፤ ለሰው የሚያስፈልገው ማናቸውም ነገር በውስጥዋ ይገኛል፤ እግዚአብሔር ይህችን አገር ለእናንተ ሰጥቶአችኋል።”
በሄዳችሁ ጊዜ ተዘልለው ወደ ተቀመጡ ሕዝብ ትደርሳላችሁ፥ ምድሪቱም ሰፊ ናት፥ እግዚአብሔርም በምድር ካለው ነገር ሁሉ አንዳች የማይጎድልበትን ስፍራ በእጃችሁ ሰጥቶአል አሉ።
ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም ሀገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊዪቱና ወደ መልካሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ ኬጤዎናውያንም፥ ወደ አሞሬዎናውያንም፥ ወደ ፌርዜዎናውያንም፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያንም፥ ወደ ኤዌዎናውያንም፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።
በዚያ ቀን ከግብፅ ምድር ወዳዘጋጀሁላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው፥ ከምድር ሁሉ ወደምትበልጥ ምድር አወጣቸው ዘንድ እጄን አነሣሁ።
በሴይር የተቀመጡ የዔሳው ልጆች፥ በአሮዔርም የተቀመጡ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ በእግሬ ልለፍ።
“አሁንም እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው፥ በሕይወትም እንድትኖሩ፥ እንድትበዙም፥ የአባቶቻችሁም አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ ዛሬ የማስተምራችሁን ሥርዐትና ፍርድ ስሙ።
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።
ሁለቱም ጐልማሶች ተመለሱ፤ ከተራራውም ወርደው ተሻገሩ፤ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ መጡ፤ የደረሰባቸውንም ሁሉ አወሩለት።
ኢያሱንም፥ “በእውነት እግዚአብሔር ሀገሩን ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶአል፤ በዚያች ምድር የሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ከእኛ የተነሣ ደነገጡ” አሉት።
እንዲህም ሆነ፤ ከተማዪቱን ሰባት ጊዜ በዞሩና ካህናቱ ቀንደ መለከቱን በነፉ ጊዜ፤ ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች አለ፥ “እግዚአብሔር ከተማዪቱን ሰጥቶአችኋልና ጩኹ።
ከዳን ወገንም የጦር ዕቃ የታጠቁ ስድስት መቶ ሰዎች ከዚያ ከሶራሕና ከእስታሔል ተነሥተው ሄዱ።
እነርሱም ሚካ የሠራውን ጣዖትና ለእርሱ የነበረውን ካህን ይዘው ወደ ሌሳ፥ ጸጥ ብሎ ተዘልሎም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ መጡ፤ በሰይፍም ስለት መቱአቸው፤ ከተማዪቱንም በእሳት አቃጠሉአት።
አምስቱም ሰዎች ሄዱ፤ ወደ ሌሳም ደረሱ፤ በውስጡም የነበሩትን ሕዝብ ተዘልለው አዩአቸው፤ እንደ ሲዶናውያንም ልማድ ጸጥ ብለው፥ ዐርፈው፥ ተዘልለውም ተቀምጠው ነበር፤ በተመዘገበች የርስታቸው ምድርም ቃልን መናገር አልቻሉም፤ ከሲዶናውያንም ርቀው ይኖሩ ነበር። ከሶርያውያንም ጋር ግንኙነት አልነበራቸውም።
እነርሱም፥ “ምድሪቱ እጅግ መልካም እንደ ሆነች አይተናል፤ ተነሡ፤ በእነርሱ ላይ እንውጣ፤ እናንተ ዝም ትላላችሁን? ትሄዱ ዘንድ፥ ምድሪቱንም ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ቸል አትበሉ።