ሚካም፥ “በእኔ ዘንድ ተቀመጥ፤ አባትና ካህንም ሁነኝ፤ እኔም ልብሶችንና ምግብህን፥ በየዓመቱም ዐሥር ብር እሰጥሃለሁ” አለው።
መሳፍንት 17:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌዋዊዉም ሄደ። ከዚያም ሰው ጋር ይኖር ዘንድ ጀመረ፤ ጐልማሳውም ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሌዋዊው ዐብሮት ለመኖር ተስማማ፤ ወጣቱም ለሚካ ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ሌዋዊው አብሮት ለመኖር ተስማማ፤ ወጣቱም ለሚካ ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወጣቱ ሌዋዊም ከሚካ ጋር ለመኖር ተስማማ፤ ያም ወጣት ካህን ለሚካ እንደ ልጅ ሆነለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌዋዊውም ከሰውዮው ጋር መቀመጥን ፈቀደ፥ ጕልማሳውም ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት። |
ሚካም፥ “በእኔ ዘንድ ተቀመጥ፤ አባትና ካህንም ሁነኝ፤ እኔም ልብሶችንና ምግብህን፥ በየዓመቱም ዐሥር ብር እሰጥሃለሁ” አለው።
ይህም ሰው በአገኘው ስፍራ ይኖር ዘንድ ከይሁዳ ከተማ ከቤተ ልሔም ሄደ፤ በዚያም ያድር ዘንድ ወደ ተራራማው ወደ ኤፍሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት ደረሰ።