La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 16:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም፥ “ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ጀምሬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናዝ​ራዊ ነኝና ራሴን ምላጭ አል​ነ​ካ​ኝም፤ የራ​ሴ​ንም ጠጕር ብላጭ ኀይሌ ከእኔ ይነ​ሣል፤ እደ​ክ​ማ​ለ​ሁም፤ እንደ ሌላም ሰው ሁሉ እሆ​ና​ለሁ” ብሎ የል​ቡን ሁሉ ነገ​ራት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ሁሉንም ነገር ነገራት፤ እንዲህም አለ፤ “ከተወለድሁ ጀምሮ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየሁ ስለ ሆንሁ ራሴን ምላጭ ነክቶት አያውቅም፤ የራሴ ጠጕር ቢላጭ ግን ኀይሌ ተለይቶኝ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ ሁሉንም ነገር ነገራት፤ እንዲህም አለ፤ “ከተወለድሁ ጀምሮ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየሁ ስለ ሆንኩ ራሴን ምላጭ ነክቶት አያውቅም፤ የራሴ ጠጉር ቢላጭ ግን ኃይሌ ተለይቶኝ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመጨረሻ እውነቱን ነገራት፤ እንዲህም አላት፦ “ከተወለድኩበት ጊዜ ጀምሮ በናዝራዊነት ለእግዚአብሔር የተለየሁ ስለ ሆነ ጠጒሬ ተላጭቶ አያውቅም፤ ጠጒሬ ቢላጭ ግን ኀይል ተለይቶኝ እንደማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም፦ ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ ለእግዚአብሔር የተለየሁ ነኝና በራሴ ላይ ምላጭ አልደረሰም፥ የራሴንም ጠጉር ብላጭ ኃይሌ ከእኔ ይሄዳል፥ እደማክለሁም፥ እንደ ሌላም ሰው እሆናለሁ ብሎ የልቡን ሁሉ ገለጠላት።

Ver Capítulo



መሳፍንት 16:17
10 Referencias Cruzadas  

ብልህ ሰው የጥበብ መንበር ነው፤ የሰነፎች ልብ ግን መርገምን ያገኛል።


አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ በከንፈሩ የሚቸኩል ግን ራሱን ይጥላል።


ባልንጀራን አትመኑ፥ በወዳጅም አትታመኑ፥ የአፍህን ደጅ በብብትህ ከምትተኛው ጠብቅ።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፤ ወንድ ወይም ሴት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን የተ​ለየ ያደ​ርግ ዘንድ ልዩ ስእ​ለት ቢሳል፥


“ራሱን ለመ​ለ​የት ስእ​ለት ባደ​ረ​ገ​በት ወራት ሁሉ ራሱን አይ​ላጭ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለ​የ​በት ወራት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ቅዱስ ይሆ​ናል፤ የራ​ሱ​ንም ጠጕር ያሳ​ድ​ጋል።


ጳው​ሎ​ስም እንደ ገና በወ​ን​ድ​ሞቹ ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀ​መጠ፤ በሰ​ላ​ምም ሸኙ​ትና ወደ ሶርያ በባ​ሕር ተጓዘ፤ ጵር​ስ​ቅ​ላና አቂ​ላም አብ​ረ​ውት ነበሩ፤ ስእ​ለ​ትም ነበ​ረ​በ​ትና በክ​ን​ክ​ራ​ኦስ ራሱን ተላጨ።


እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ልጁም ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን ጀምሮ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ናዝ​ራዊ ይሆ​ና​ልና በራሱ ላይ ምላጭ አይ​ድ​ረ​ስ​በት፤ እር​ሱም እስ​ራ​ኤ​ልን ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ማዳን ይጀ​ም​ራል።”


ከዚ​ህም በኋላ ሌሊ​ቱን ሁሉ በነ​ገር በዘ​በ​ዘ​በ​ች​ውና በአ​ደ​ከ​መ​ችው ጊዜ፥ ልሙት እስ​ኪል ድረስ ተበ​ሳጨ።


ደሊ​ላም የል​ቡን ሁሉ እንደ ነገ​ራት ባወ​ቀች ጊዜ፥ “የል​ቡን ሁሉ ነግ​ሮ​ኛ​ልና ይህን ጊዜ ደግሞ ኑ” ብላ ላከ​ችና የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መሳ​ፍ​ንት ጠራች። የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መሳ​ፍ​ንት ብሩን በእ​ጃ​ቸው ይዘው ወደ እር​ስዋ መጡ።