መሳፍንት 16:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ሥራ ባልተሠራባቸው ሰባት አዳዲስ ገመዶች ቢያስሩኝ፥ እደክማለሁ፤ እንደ ሌላውም ሰው እሆናለሁ” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ሥራ ላይ ባልዋሉ አዳዲስ ገመዶች ቢያስሩኝ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፥ “ሥራ ላይ ባልዋሉ አዳዲስ ገመዶች ቢያስሩኝ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “ሥራ ባልተሠራበት አዲስ ገመድ ቢያስሩኝ እንደማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” ሲል መለሰላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ሥራ ባልተሠራበት በአዲስ ገመድ ቢያስሩኝ፥ እደክማለሁ፥ እንደ ሌላም ሰው እሆናለሁ አላት። |
እነርሱም፥ “በገመድ አስረን በእጃቸው አሳልፈን እንሰጥሃለን እንጂ አንገድልህም” ብለው ማሉለት። በሁለትም አዲስ ገመድ አስረው ከዓለቱ ውስጥ አወጡት።
ደሊላም ሶምሶንን፥ “እነሆ፥ አታለልኸኝ፤ የነገርኸኝም ሐሰት ነው፤ አሁንም የምትታሰርበት ምን እንደሆነ፥ እባክህ ንገረኝ” አለችው።
ደሊላም ሰባት አዳዲስ ገመዶች ወስዳ በእነርሱ አሰረችው፤ የሚያደቡትም ሰዎች በጓዳዋ ውስጥ ተቀምጠው ነበር። እርስዋም፥ “ሶምሶን ሆይ! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ገመዶችንም ከክንዱ እንደ ፈትል በጣጠሳቸው።