መሳፍንት 16:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደሊላም ሶምሶንን፥ “እነሆ፥ አታለልኸኝ፤ የነገርኸኝም ሐሰት ነው፤ አሁንም የምትታሰርበት ምን እንደሆነ፥ እባክህ ንገረኝ” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደሊላም ሳምሶንን፣ “አሞኝተኸኛል፤ ዋሽተኸኛል፤ እባክህ አሁንም አንተን እንዴት ማሰር እንደሚቻል ንገረኝ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደሊላም ሳምሶንን፥ “አሞኝተኸኛል፤ ዋሽተኸኛል፤ እባክህ አሁንም አንተን እንዴት ማሰር እንደሚቻል ንገረኝ” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደሊላም ሶምሶንን “እነሆ! አታለልከኝ፤ እውነቱንም አልነገርከኝም፤ አሁንም አንተን እንዴት ማሰር እንደሚቻል እባክህ ንገረኝ!” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደሊላም ሶምሶንን፦ እነሆ፥ አታለልኸኝ፥ የነገርኸኝም ሀሰት ነው፥ አሁንም የምትታሰርበት ምን እንደ ሆነ፥ እባክህ፥ ንገረኝ አለችው። |
ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፤ ቃልህንም ይሰማሉ፤ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባቸውም ጣዖታትን ይከተላልና።
እርሱም፥ “ሥራ ባልተሠራባቸው ሰባት አዳዲስ ገመዶች ቢያስሩኝ፥ እደክማለሁ፤ እንደ ሌላውም ሰው እሆናለሁ” አላት።
ደሊላም ሶምሶንን፥ “እስከ አሁን ድረስ አታለልኸኝ፤ የነገርኸኝም ሐሰት ነው፤ የምትታሰርበት ምን እንደሆነ ንገረኝ” አለችው። እርሱም፥ “የራሴን ጠጕር ሰባቱን ጕንጕን ከድር ጋር ብትጐነጕኚው፥ በግድግዳም ላይ በችካል ብትቸክዪው፥ ከሰዎች እንደ አንዱ እደክማለሁ፥” አላት።
የሚያደቡትም ሰዎች በጓዳዋ ውስጥ ተደብቀው ነበር። እርስዋም፥ “ሶምሶን ሆይ! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። እርሱም ፈትል እሳት በሸተተው ጊዜ እንዲበጠስ ጠፍሩን በጣጠሰው፤ ኀይሉም በምን እንደ ሆነ አልታወቀም።