መሳፍንት 15:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መናገሩንም በፈጸመ ጊዜ መንጋጋውን ከእጁ ጣለ፤ የዚያንም ስፍራ ስም “ቀትለ አጽመ መንሰክ” ብሎ ጠራው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ተናግሮ እንዳበቃ የአህያውን መንጋጋ ከእጁ ወዲያ ወረወረው፤ የዚያም ቦታ ስም ራማት ሌሒ ተብሎ ተጠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ተናግሮ እንዳበቃ የአህያውን መንጋጋ ከእጁ ወዲያ ወረወረው፤ የዚያም ቦታ ስም ራማት ሌሒሰ ተብሎ ተጠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ይዞት የነበረውን መንጋጋ ወረወረው፤ ይህም የተፈጸመበት ያ ስፍራ “ራማት ሌሒ” ተብሎ ተጠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መናገሩንም በፈጸመ ጊዜ መንጋጋውን ከእጁ ጣለ፥ የዚያንም ስፍራ ስም ራማትሌሒ ብሎ ጠራው። |
ሶምሶንም፥ “በአህያ መንጋጋ አጥንት ክምር በክምር ላይ አድርጌአቸዋለሁ፤ በአህያ መንጋጋ አጥንት አንድ ሺህ ሰው ገድያለሁና” አለ።
እርሱም እጅግ ተጠምቶ ነበርና፥ “አንተ ይህችን ታላቅ ማዳን በባሪያህ እጅ ሰጥተሃል፤ አሁንም በጥም እሞታለሁ፤ ባልተገረዙትም እጅ እወድቃለሁ” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።