መሳፍንት 15:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሶምሶንም፥ “በአህያ መንጋጋ አጥንት ክምር በክምር ላይ አድርጌአቸዋለሁ፤ በአህያ መንጋጋ አጥንት አንድ ሺህ ሰው ገድያለሁና” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳምሶንም፣ “በአንድ የአህያ መንጋጋ፣ ሺሕ ሰው ዘራሪ፤ በአንድ የአህያ መንጋጋ፣ ሺሕ ሬሳ አነባባሪ” ብሎ ፎከረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳምሶንም፥ “በአንድ የአህያ መንጋጋ፥ ሺህ ሰው ዘራሪ፤ በአንድ የአህያ መንጋጋ፥ ሺህ ሬሳ አነባባሪ!” ብሎ ፎከረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሶምሶንም፥ “በአህያ መንጋጋ አንድ ሺህ ሰው ገደልኩ፤ በዚህም የአህያ መንጋጋ ሬሳውን በሬሳ ላይ ከመርሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሶምሶንም፦ በአህያ መንጋጋ ክምር በክምር ላይ አድርጌአቸዋለሁ፥ በአህያ መንጋጋ አንድ ሺህ ሰው ገድያለሁ አለ። |
ሕዝቡም ሁሉ ባዩት ጊዜ፥ “ምድራችንን ያጠፋውን፥ ከእኛም ብዙ ሰው የገደለውን ጠላታችንን አምላካችን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን እያሉ አምላካቸውን አመሰገኑ።