መሳፍንት 15:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “በገመድ አስረን በእጃቸው አሳልፈን እንሰጥሃለን እንጂ አንገድልህም” ብለው ማሉለት። በሁለትም አዲስ ገመድ አስረው ከዓለቱ ውስጥ አወጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “አስረን ብቻ ለእነርሱ አሳልፈን እንሰጥሃለን እንጂ ራሳችን አንገድልህም” አሉት፤ ከዚያ በሁለት አዳዲስ ገመድ አስረው ከዐለቱ ዋሻ አወጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፥ “አስረን ብቻ ለእነርሱ አሳልፈን እንሰጥሃለን እንጂ ራሳችን አንገድልህም” አሉት፤ ከዚያ በሁለት አዳዲስ ገመድ አስረው ከዐለቱ ዋሻ አወጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “መልካም ነው፤ አንተን በገመድ አስረን ለእነርሱ አሳልፈን እንሰጥሃለን እንጂ እኛስ አንገድልህም” ሲሉ መለሱለት። ከዚህም በኋላ በሁለት አዳዲስ ገመዶች አሰሩትና ከዋሻው አውጥተው ወሰዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ አስረን በእጃቸው አሳልፈን እንሰጥሃለን እንጂ አንገድልህም ብለው ተናገሩት። በሁለትም አዲስ ገመድ አስረው ከዓለቱ ውስጥ አወጡት። |
እነርሱም፥ “አስረን በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፈን ልንሰጥህ መጥተናል” አሉት። ሶምሶንም፥ “እናንተ እንዳትገድሉኝ ማሉልኝ፤ ለእነርሱም አሳልፋችሁ ስጡኝ፤ እናንተ ግን ከእኔ ጋር አትዋጉ” አላቸው።
የአህያ መንጋጋ አጥንት ወደ ተባለ ቦታም ደረሰ፤ ፍልስጥኤማውያንም ደንፍተው ተቀበሉት፤ ወደ እርሱም ሮጡ። የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ በክንዱም ያሉ እነዚያ ገመዶች በእሳት ላይ እንደ ተጣለ ገለባ ሆኑ፤ ማሰሪያውም ከክንዱ ተፈታ፤
እርሱም፥ “ሥራ ባልተሠራባቸው ሰባት አዳዲስ ገመዶች ቢያስሩኝ፥ እደክማለሁ፤ እንደ ሌላውም ሰው እሆናለሁ” አላት።