የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ የፍየል ጠቦትን እንደሚጥልም ጣለው፤ በእጁም እንደ ኢምንት ሆነ፤ ያደረገውንም ለአባቱና ለእናቱ አልተናገረም።
መሳፍንት 14:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሂደውም ከሴቲቱ ጋር ተነጋገሩ፤ ሶምሶንንም በፊቱ ደስ አሰኘችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ሴቲቱም ወረደ፤ ከርሷም ጋራ ተነጋገረ፤ እጅግም ወደዳት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሴቲቱም ወረደ፤ ከእርሷም ጋር ተነጋገረ፤ እጅግም ወደዳት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ወደ ሴቲቱ ሄዶ አነጋገራት፤ ወደዳትም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወርዶም ከሴቲቱ ጋር ተነጋገረ፥ እጅግም ደስ አሰኘችው። |
የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ የፍየል ጠቦትን እንደሚጥልም ጣለው፤ በእጁም እንደ ኢምንት ሆነ፤ ያደረገውንም ለአባቱና ለእናቱ አልተናገረም።
ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ሊያገባት ተመለሰ፤ የአንበሳውንም ሬሳ ያይ ዘንድ ከመንገድ ፈቀቅ አለ፤ እነሆም፥ በአንበሳው አፍ ውስጥ ንብ ሰፍሮበት ነበር፤ ማርም ነበረበት።