እኅቴ ሙሽሪት ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከርቤዬን ከሽቱዬ ጋር ለቀምሁ፥ እንጀራዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወይን ጠጄን ከወተቴ ጋር ጠጣሁ። ባልንጀሮች በሉ፥ ጠገቡም፤ የወንድሞች ልጆች ጠጡ፥ ሰከሩም፥ ልባቸው የጠፋ ነውና።
መሳፍንት 14:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሶምሶንም ሚስት ከስር ሚዜው ጋር ተቀመጠች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳምሶንም ሚስት ለሚዜው ተዳረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳምሶንም ሚስት ለሚዜው ተዳረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስቱም በሠርጉ ሚዜ ለነበረው ጓደኛው ተዳረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሶምሶን ሚስት ግን ከተባበሩት ከሚዜዎቹ ለአንደኛው ሆነች። |
እኅቴ ሙሽሪት ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከርቤዬን ከሽቱዬ ጋር ለቀምሁ፥ እንጀራዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወይን ጠጄን ከወተቴ ጋር ጠጣሁ። ባልንጀሮች በሉ፥ ጠገቡም፤ የወንድሞች ልጆች ጠጡ፥ ሰከሩም፥ ልባቸው የጠፋ ነውና።
እያንዳንዱ በባልንጀራው ላይ ይሣለቃል በእውነትም አይናገርም፤ ሐሰት መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፤ በደሉ መመለስንም እንቢ አሉ።
ነገር ግን ይህን የምናገር ስለ ሁላችሁ አይደለም፤ የመረጥኋቸው እነማን እንደ ሆኑ እኔ አውቃለሁ፤ ነገር ግን መጽሐፍ ‘እንጀራዬን የሚመገብ ተረከዙን በእኔ ላይ አነሣ’ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።
ሙሽራ ያለችው ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው የሙሽራው ሚዜ ግን በሙሽራው ቃል እጅግ ደስ ይለዋል፤ የእኔ ደስታ አሁን ተፈጸመች።
አባቷም፥ “ፈጽመህ ጠላህዋት ያልህ መስሎኝ ለሚዜህ አጋባኋት፤ ታናሽ እኅቷ ከእርስዋ ይልቅ የተዋበች አይደለችምን? እባክህ በእርስዋ ፋንታ አግባት” አለው።
ፍልስጥኤማውያንም፥ “ይህን ያደረገ ማን ነው?” አሉ። እነርሱም፥ “ሚስቱን ወስዶ ለሚዜው አጋብቶበታልና የቴምናታዊዉ አማች ሶምሶን ነው” አሉአቸው። ፍልስጥኤማውያንም ወጥተው የአባቷን ቤትና እርስዋን አባቷንም በእሳት አቃጠሉ።