ይሁዳም ጋዛንና አውራጃዋን፥ አስቀሎናንና አውራጃዋን፥ አቃሮንንና አውራጃዋን፥ አዛጦንንና አውራጃዋን አልወረሳትም።
መሳፍንት 14:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ ወረደ፤ ወደ አስቀሎናም ወረደ፤ ከዚያም ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፤ ልብሳቸውንም ገፍፎ እንቆቅልሹን ለነገሩት ሰዎች ሰጠ። ሶምሶንም ተቈጣ፤ ወደ አባቱም ቤት ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የእግዚአብሔር መንፈስ በሳምሶን ላይ በኀይል ወረደበት፤ ወደ አስቀሎናም ወርዶ ከሰዎቻቸው መካከል ሠላሳውን ገደለ፤ ያላቸውንም ከገፈፈ በኋላ ልብሶቻቸውን አምጥቶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጣቸው። በቍጣ እንደ ነደደም ተነሥቶ ወደ አባቱ ቤት ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም የጌታ መንፈስ በሳምሶን ላይ በኃይል ወረደበት፤ ወደ አስቀሎናም ወርዶ ከሰዎቻቸው መካከል ሠላሳውን ገደለ፤ ያላቸውንም ከገፈፈ በኋላ ልብሶቻቸውን አምጥቶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጣቸው። በቁጣ እንደነደደም ተነሥቶ ወደ አባቱ ቤት ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርም መንፈስ ለእርሱ ብርታትን ሰጠው፤ ወደ አስቀሎናም ወርዶ ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፤ ውብ የሆነውንም ልብሳቸውን ሁሉ በመግፈፍ አምጥቶ የእንቆቅልሹን ፍች ላወቁት ሰዎች ሰጣቸው። በሆነውም ነገር ሁሉ እጅግ ተቈጥቶ ወደ ቤተሰቦቹ ተመለሰ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ በኃይል ወረደ፥ ወደ አስቀሎናም ወረደ፥ ከዚያም ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፥ ልብሳቸውንም ወስዶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጠ። ቁጣውም ነደደ፥ ወደ አባቱም ቤት ወጣ። |
ይሁዳም ጋዛንና አውራጃዋን፥ አስቀሎናንና አውራጃዋን፥ አቃሮንንና አውራጃዋን፥ አዛጦንንና አውራጃዋን አልወረሳትም።
በሰባተኛዪቱም ቀን ፀሐይ ሳትገባ የከተማዪቱ ሰዎች፥ “ከማር የሚጣፍጥ ምንድን ነው? ከአንበሳስ የሚበረታ ማን ነው?” አሉት። ሶምሶንም፥ “በጥጃዬ ባላረሳችሁ ኑሮ የእንቆቅልሼን ትርጓሜ ባላወቃችሁም ነበር” አላቸው።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ የፍየል ጠቦትን እንደሚጥልም ጣለው፤ በእጁም እንደ ኢምንት ሆነ፤ ያደረገውንም ለአባቱና ለእናቱ አልተናገረም።
የአህያ መንጋጋ አጥንት ወደ ተባለ ቦታም ደረሰ፤ ፍልስጥኤማውያንም ደንፍተው ተቀበሉት፤ ወደ እርሱም ሮጡ። የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ በክንዱም ያሉ እነዚያ ገመዶች በእሳት ላይ እንደ ተጣለ ገለባ ሆኑ፤ ማሰሪያውም ከክንዱ ተፈታ፤
የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ በእስራኤልም ላይ ይፈርድ ነበር፤ ለጦርነትም ወጣ፤ እግዚአብሔርም በወንዞች መካከል ያለች የሶርያ ንጉሥ ኩሳርሳቴምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እጁም በኩሳርሳቴም ላይ በረታች።
ፍልስጥኤማውያንም ስለ በደል መባእ ለእግዚአብሔር ያቀረቡአቸው የሰውነታቸው ምሳሌ የወርቅ እባጮች እነዚህ ናቸው፦ አንዲቱ ለአዛጦን፥ አንዲቱም ለጋዛ፥ አንዲቱም ለአስቀሎና፥ አንዲቱም ለጌት፥ አንዲቱም ለአቃሮን።
እነርሱም፥ “ስለ መቅሠፍቱ የምንሰጠው የበደል መባእ ምንድን ነው?” አሉ። እነርሱም እንዲህ አሉ፥ “እናንተንና አለቆቻችሁን፥ ሕዝባችሁንም ያገኘች መቅሠፍት አንዲት ናትና እንደ ፍልስጥኤማውያን አለቆች ቍጥር አምስት የወርቅ እባጮች፥ አምስትም የወርቅ አይጦች አቅርቡ።