ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፥ ለዐይንም ለማየት እንደሚያስጐመጅ፥ መልካምንም እንደሚያሳውቅ ባየች ጊዜ፥ ከፍሬው ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።
መሳፍንት 14:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባቱንም የበዓል ቀን አለቀሰችበት፤ እርስዋም ነዝንዛዋለችና በሰባተኛው ቀን ነገራት። ለሕዝብዋም ልጆች ነገረቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚስቱም በሰርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ እያለቀሰች ጨቀጨቀችው፤ አጥብቃ ስለ ነዘነዘችውም በመጨረሻ በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርሷም በበኩሏ የዕንቈቅልሹን ፍች ለሕዝቧ ነገረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚስቱም በሰርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ እያለቀሰች ጨቀጨቀችው፤ አጥብቃ ስለ ነዘነዘችውም በመጨረሻ በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርሷም በበኩሏ የእንቈቅልሹን ፍች ለሕዝቧ ነገረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም የተነሣ እርስዋ በሠርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ አለቀሰች፤ አጥብቃም ስለ ነዘነዘችው የእንቆቅልሹን ፍች በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርስዋም ሄዳ ለፍልስጥኤማውያኑ ነገረቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባቱንም የበዓል ቀን በፊቱ አለቀሰች፥ እርስዋም ነዝንዛዋለችና በሰባተኛው ቀን ነገራት። ትርጓሜውንም ለሕዝብዋ ልጆች ነገረች። |
ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፥ ለዐይንም ለማየት እንደሚያስጐመጅ፥ መልካምንም እንደሚያሳውቅ ባየች ጊዜ፥ ከፍሬው ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።
ብዙ ወራትም ካለፈ በኋላ ሚስቱ እንዲህ አለችው፥ “እስከ መቼ ትታገሣለህ? 9 ‘ሀ’ ዳግመኛም እግዚአብሔርን ጥቂት ወራት ደጅ እጠናዋለሁ፤ ዳግመኛም መከራውን እታገሠዋለሁ፤ የቀድሞው ኑሬዬንም ተስፋ አደርገዋለሁ ትላለህን? 9 ‘ለ’ እንደዚህስ እንዳትል ከዚህ ዓለም እነሆ ስም አጠራርህ ጠፋ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቼም ሞቱ፥ ማኅፀኔም በምጥ ተጨነቀ፥ በከንቱም ደከምሁ። 9 ‘ሐ’ አንተም በመግልና በትል ትኖራለህ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ትዛብራለህ። 9 ‘መ’ እኔ ግን እየዞርሁ እቀላውጣለሁ። ከአንዱ መንደር ወደ አንዱ መንደር፥ ከአንዱ ቤትም ወደ አንዱ ቤት እሄዳለሁ፤ ከድካሜና በእኔ ላይ ካለ ችግሬም ዐርፍ ዘንድ ፀሐይ እስኪገባ ድረስ እጠብቃለሁ፤ ነገር ግን አሁን እግዚአብሔርን ስደብና ሙት።”
“ምላሳቸውን ለሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድርም በረቱ፤ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥” ይላል እግዚአብሔር።
የሶምሶንም ሚስት በፊቱ እያለቀሰችበት፥ “ጠልተኸኛል፤ ከቶም አትወድደኝም፤ ለሕዝቤ ልጆች የነገርኸውን እንቆቅልሽህን አልነገርኸኝምና” አለችው። እርሱም፥ “እነሆ፥ ለአባቴና ለእናቴ አልነገርኋቸውም፤ ለአንቺ እነግርሻለሁን?” አላት።
በሰባተኛዪቱም ቀን ፀሐይ ሳትገባ የከተማዪቱ ሰዎች፥ “ከማር የሚጣፍጥ ምንድን ነው? ከአንበሳስ የሚበረታ ማን ነው?” አሉት። ሶምሶንም፥ “በጥጃዬ ባላረሳችሁ ኑሮ የእንቆቅልሼን ትርጓሜ ባላወቃችሁም ነበር” አላቸው።
ደሊላም ሶምሶንን፥ “እስከ አሁን ድረስ አታለልኸኝ፤ የነገርኸኝም ሐሰት ነው፤ የምትታሰርበት ምን እንደሆነ ንገረኝ” አለችው። እርሱም፥ “የራሴን ጠጕር ሰባቱን ጕንጕን ከድር ጋር ብትጐነጕኚው፥ በግድግዳም ላይ በችካል ብትቸክዪው፥ ከሰዎች እንደ አንዱ እደክማለሁ፥” አላት።