መሳፍንት 14:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሶምሶንም ሚስት በፊቱ እያለቀሰችበት፥ “ጠልተኸኛል፤ ከቶም አትወድደኝም፤ ለሕዝቤ ልጆች የነገርኸውን እንቆቅልሽህን አልነገርኸኝምና” አለችው። እርሱም፥ “እነሆ፥ ለአባቴና ለእናቴ አልነገርኋቸውም፤ ለአንቺ እነግርሻለሁን?” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ የሳምሶን ሚስት ተንሰቅስቃ እያለቀሰች ከፊቱ በመቅረብ፣ “ለካስ ትጠላኛለህ! በርግጥ አትወድደኝም” አለችው። እርሱም፣ “ይህን ለአባቴም ሆነ ለእናቴ አልነገርኋቸውም፤ ታዲያ ለአንቺ ለምን እነግርሻለሁ?” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ የሳምሶን ሚስት ተንሰቅስቃ እያለቀሰች ከፊቱ በመቅረብ፥ “ለካስ ትጠላኛለህ በእርግጥ አትወደኝም” አለችው። እርሱም፥ “ይህን ለአባቴም ሆነ ለእናቴ አልነገርኋቸውም፤ ታዲያ ለአንቺ ለምን እነግርሻለሁ?” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የሶምሶን ሚስት እያለቀሰች ወደ እርሱ ቀርባ “ለካስ አንተ እኔን አትወደኝም! እንዲያውም በጣም ትጠላኛለህ! የአገሬን ልጆች እንቆቅልሽ ጠይቀህ ለእኔ እስከ አሁን ፍቺውን አልነገርከኝም!” አለችው። እርሱም “እነሆ! እኔ ይህን ለአባቴና ለእናቴ እንኳ አልነገርኳቸውም፤ ታዲያ ለአንቺ የምነግርበት ምክንያት ምንድን ነው?” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሶምሶንም ሚስት በፊቱ እያለቀሰች፦ በእውነት ጠልተኸኛል፥ ከቶም አትወድደኝም፥ ለሕዝቤ ልጆች እንቈቅልሽ ሰጥተሃቸዋልና ትርጓሜውንም አልነገርኸኝም አለችው። እርሱም፦ እነሆ፥ ለአባቴና ለእናቴ አልነገርኋቸውም፥ ለአንቺ እነግርሻለሁን? አላት። |
ሰባቱንም የበዓል ቀን አለቀሰችበት፤ እርስዋም ነዝንዛዋለችና በሰባተኛው ቀን ነገራት። ለሕዝብዋም ልጆች ነገረቻቸው።
ደሊላም፥ “ ‘አንተ እወድድሻለሁ’ እንዴት ትለኛለህ? ልብህ ከእኔ ጋር አይደለም፤ ስታታልለኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው፥ ታላቅ ኀይልህም በምን እንደ ሆነ አልነገርኸኝም” አለችው።