መሳፍንት 14:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቱም ወደ ሴቲቱ ወረደ፤ ጐበዞችም እንዲሁ ያደርጉ ነበርና ሶምሶን በዚያ ሰባት ቀን በዓል አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳምሶን አባት ልጅቱን ሊያይ ወረደ፤ ሳምሶንም በነበረው የሙሽራ ወግ መሠረት በዚያ ግብዣ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳምሶን አባት ልጅቱን ሊያይ ወረደ፤ ሳምሶንም በወጣቶች የተለመደ በነበረው መሠረት በዚያ ግብዣ አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቱ ወደ ሴቲቱ ቤት በሄደ ጊዜ፥ ሶምሶን በዚያ ትልቅ ግብዣ አደረገ፤ ይህም ዐይነቱ ግብዣ በወጣቶች ዘንድ የተለመደ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቱም ወደ ሴቲቱ ወረደ፥ ጎበዞችም እንዲህ ያደርጉ ነበርና ሶምሶን በዚያ በዓል አደረገ። |
አሳዳሪውም ያን የወይን ጠጅ የሆነውን ውኃ ቀምሶ አደነቀ፤ ከወዴት እንደ መጣም አላወቀም፤ የቀዱት አሳላፊዎች ግን የወይን ጠጅ የሆነውን ያን ውኃ ያውቁ ነበር። ውኃዉን የሞሉ እነርሱ ነበሩና።
ወስዶም በላ፤ እየበላም ሄደ፤ ወደ አባቱና ወደ እናቱም ደረሰ፤ ሰጣቸውም፤ እነርሱም በሉ፤ ማሩንም ከአንበሳው አፍ ውስጥ እንዳወጣው አልነገራቸውም።