መሳፍንት 13:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መንፈስ በሶራሕና በእስታሔል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ከእርሱ ጋር ይሄድ ጀመረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ሳለ ያነቃቃው ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ሳለ ያነቃቃው ጀመር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ በነበረበት ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ ያበረታው ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ሊያነቃቃው ጀመረ። |
የእግዚአብሔርም መንፈስ በዮፍታሔ ላይ መጣ፤ እርሱም የምናሴ ዕጣ ከምትሆን ከገለዓድ ምድርና ከገለዓድ መሴፋ፥ ወደ አሞን ልጆች ማዶ ተሻገረ።
ሶምሶንም ወደ ቴምናታ ወረደ፤ በቴምናታም ከፍልስጥኤማውያን ልጆች አንዲት ሴት አየ፤ እርስዋም በፊቱ ደስ አለችው።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ ወረደ፤ ወደ አስቀሎናም ወረደ፤ ከዚያም ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፤ ልብሳቸውንም ገፍፎ እንቆቅልሹን ለነገሩት ሰዎች ሰጠ። ሶምሶንም ተቈጣ፤ ወደ አባቱም ቤት ተመለሰ።
ወንድሞቹም፥ የአባቱ ቤተ ሰቦችም ሁሉ ወረዱ፤ ይዘውም አመጡት፤ በሶሬሕና በኢስታሔል መካከል ባለው በአባቱ በማኑሄ መቃብር ቀበሩት። እርሱም እስራኤልን ሃያ ዓመት ገዛቸው።
የዳንም ልጆች ከወገናቸው አምስት ጽኑዓን ሰዎች ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲመረምሩ፥ “ሂዱ ምድሪቱንም ሰልሉ” ብለው ከሶራሕና ከኢስታሔል ላኩ። እነዚያም ወደ ተራራማዉ ወደ ኤፍሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት መጥተው በዚያ አደሩ።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ በእስራኤልም ላይ ይፈርድ ነበር፤ ለጦርነትም ወጣ፤ እግዚአብሔርም በወንዞች መካከል ያለች የሶርያ ንጉሥ ኩሳርሳቴምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እጁም በኩሳርሳቴም ላይ በረታች።