መሳፍንት 13:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማኑሄም የእግዚአብሔርን መልአክ፥ “ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማኑሄ የእግዚአብሔርን መልአክ፣ “የተናገርኸው ሲፈጸም እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” በማለት ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማኑሄ የጌታን መልአክ፥ “የተናገርከው ሲፈጸም እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” በማለት ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማኑሄም “የተናገርከው ቃል ሲፈጸም ምስጋና እናቀርብልህ ዘንድ ስምህ ማን ነው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኑሄም የእግዚአብሔርን መልአክ፦ ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው? አለው። |
በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፥ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰውነቴም ዳነች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ራእየ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው።