የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፥ “እነሆ፥ አንቺ መካን ነሽ፤ ልጅም አልወለድሽም፤ ነገር ግን ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ።
መሳፍንት 13:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማኑሄም የእግዚአብሔርን መልአክ፥ “የፍየል ጠቦት እናዘጋጅልህ ዘንድ ግድ እንልሃለን” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ማኑሄ የእግዚአብሔርን መልአክ፣ “የፍየል ጠቦት ዐርደን እስክናዘጋጅልህ ድረስ እባክህ ቈይ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ማኑሄ የጌታን መልአክ “የፍየል ጠቦት ዐርደን እስክናዘጋጅልህ ድረስ እባክህ ቈይ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማኑሄም የእግዚአብሔርን መልአክ “አንድ የፍየል ጠቦት ዐርደን እስክናዘጋጅልህ ድረስ እባክህ ቈይልን!” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኑሄም የእግዚአብሔርን መልአክ፦ የፍየል ጠቦት እስክናዘጋጅልህ ድረስ፥ እባክህ፥ ቆይ አለው። |
የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፥ “እነሆ፥ አንቺ መካን ነሽ፤ ልጅም አልወለድሽም፤ ነገር ግን ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ።
የእግዚአብሔርም መልአክ፥ “ሥጋውንና የቂጣውን እንጎቻ ወስደህ በዚህ ድንጋይ ላይ አኑር፤ መረቁንም አፍስስ” አለው። እንዲሁም አደረገ።