መሳፍንት 11:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ሂጂ” አለ። ሁለት ወርም አሰናበታት፤ ከባልንጀሮችዋም ጋር ሄደች፤ በተራሮችም ላይ ለድንግልናዋ አለቀሰች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “በይ ሂጂ” ብሎ ለሁለት ወር አሰናበታት፤ እርሷም ከእንግዲህ ባል ስለማታገባ ከልጃገረድ ጓደኞቿ ጋራ ወደ ተራሮች ሄደው አለቀሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፥ “በይ ሂጂ” ብሎ ለሁለት ወር አሰናበታት፤ እርሷም ከእንግዲህ ባል ስለማታገባ ከልጃገረድ ጓደኞቿ ጋር ወደ ተራሮች ሄደው አለቀሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም እንድትሄድ ፈቅዶ ለሁለት ወር አሰናበታት፤ እርስዋና ጓደኞችዋም ወደ ተራራዎች ወጡ፤ ከዚያም ባል አግብታ ልጆች የማትወልድ በመሆንዋ አለቀሱላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ሂጂ አለ። ሁለት ወርም አሰናበታት፥ ከባልንጀሮችዋም ጋር ሄደች፥ በተራሮችም ላይ ለድንግልናዋ አለቀሰች። |
አባቷንም፥ “ይህ ነገር ይደረግልኝ፤ ከዚህ ሄጄ በተራሮች ላይ እንድወጣና እንድወርድ፥ ከባልንጀሮቼም ጋር ለድንግልናዬ እንዳለቅስ ሁለት ወር አሰናብተኝ” አለችው።
ሁለት ወርም ከተፈጸመ በኋላ ወደ አባቷ ተመለሰች፤ ዮፍታሔም የተሳለውን ስእለት አደረገ፤ እርስዋም ወንድ አላወቀችም ነበር።