ሦራም አብራምን፥ “ከአንተ የተነሣ እገፋለሁ፤ እኔ አገልጋዬን በብብትህ ሰጠሁህ፤ እንደ ፀነሰችም ባየች ጊዜ እኔን ማክበርን ተወች፤ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ” አለችው።
መሳፍንት 11:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ አልበደልሁህም፤ አንተ ግን ከእኔ ጋር ትዋጋ ዘንድ ክፉ አታድርግብኝ፤ ፈራጁ እግዚአብሔር በእስራኤል ልጆችና በአሞን ልጆች መካከል ዛሬ ይፍረድ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ አልበደልሁህም፤ አንተ ግን በእኔ ላይ ዘምተህ በድለኸኛል፤ እንግዲህማ ፈራጁ እግዚአብሔር በእስራኤላውያንና በአሞናውያን መካከል ዛሬ ይፍረድ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ አልበደልሁህም፤ አንተ ግን በእኔ ላይ ዘምተህ በድለኸኛል፤ እንግዲህማ ፈራጅ የሆነው ጌታ በእስራኤላውያንና በአሞናውያን መካከል ዛሬ ይፍረድ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ በበኩሌ ምንም አልበደልኩም፤ በእኔ ላይ ጦርነት በመክፈት ልትበድለኝ የተነሣሣህ አንተ ነህ፤ እንግዲህ ፈራጅ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ ዛሬ በእስራኤላውያንና በዐሞናውያን መካከል ውሳኔ ይሰጣል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ አልበደልሁህም፥ አንተ ግን ከእኔ ጋር እየተዋጋህ በድለኸኛል፥ ፈራጁ እግዚአብሔር በእስራኤል ልጆችና በአሞን ልጆች መካከል ዛሬ ይፍረድ። |
ሦራም አብራምን፥ “ከአንተ የተነሣ እገፋለሁ፤ እኔ አገልጋዬን በብብትህ ሰጠሁህ፤ እንደ ፀነሰችም ባየች ጊዜ እኔን ማክበርን ተወች፤ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ” አለችው።
አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።”
አንተም ወደ እኔ ብታልፍ የአብርሃም አምላክ የናኮርም አምላክ በእኛ መካከል ይፍረድ።” ያዕቆብም በአባቱ በይስሐቅ አምላክ ማለ።
አምላካችን ሆይ፥ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን መቃወም እንችል ዘንድ ኀይል የለንም፤ የምናደርግባቸውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዐይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው።”
አምላካችን እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፥ በተቀደሰው ተራራ ይሰግዱለታል፤ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።
አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ፥ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ ዕወቅ።
መልካም ቢሆን፥ ክፉም ቢሆን በሥጋችን እንደ ሠራነው ዋጋችንን እንቀበል ዘንድ፥ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለንና።
ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።
ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈ ወደ ማኅበረ በኵርም፥ ሁሉን ወደሚገዛም ወደ እግዚአብሔር፥ ወደ ፍጹማን ጻድቃንም ነፍሳት፥
እግዚአብሔር ጠላቶቹን ያደክማቸዋል፤ እግዚአብሔር ብቻ ቅዱስ ነው፤ ጥበበኛ በጥበቡ አይመካ፤ ኀይለኛም በኀይሉ አይመካ፤ ሀብታምም በሀብቱ አይመካ፤ የሚመካ ግን በዚህ ይመካ፤ እግዚአብሔርን በማወቅና በማስተዋል፤ በምድርም መካከል ፍርድንና እውነትን በማድረግ፥ እግዚአብሔር ወደ ሰማይ ወጣ፤ አንጐደጐደም። ጻድቅ እርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሦቻችንም ኀይልን ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”
እነሆ፥ የልብስህ ዘርፍ በእጄ እንዳለ ተመልክተህ ዕወቅ፤ የልብስህንም ዘርፍ በቈረጥሁ ጊዜ አልገደልሁህም፤ ስለዚህም በእጄ ክፋት፥ በደልና ክዳት እንደሌለ፥ አንተንም እንዳልበደልሁህ ዕወቅ፤ አንተ ግን ነፍሴን ልታጠፋ ታጠምዳለህ።
እግዚእብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ፤ እግዚአብሔርም አንተን ይበቀልልኝ፤ እጄ ግን በአንተ ላይ አትሆንም።
አሁንም የእስራኤል ንጉሥ ማንን ለማሳደድ ወጥተሀል? አንተስ ማንን ታሳድዳለህ? የሞተ ውሻን ታሳድዳለህን? ወይስ ቍንጫን ታሳድዳለህ?
እንግዲህ እግዚአብሔር ዳኛ ይሁን፤ በእኔና በአንተም መካከል ይፍረድ፤ አይቶም ለእኔ ይፍረድ፤ ከእጅህም ያድነኝ።”